ኢዮብ 27:1-23
27 ኢዮብ ንግግሩን* በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2 “ፍትሕ በነፈገኝ ሕያው በሆነው አምላክ፣+እንድመረር ባደረገኝ*+ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ እምላለሁ፤
3 እስትንፋሴ በውስጤ፣ከአምላክ ያገኘሁትም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ እስካለ ድረስ፣+
4 ከንፈሮቼ ክፋት አይናገሩም፤ምላሴም ፈጽሞ የማታለያ ቃል አይወጣውም!
5 በእኔ በኩል እናንተን ጻድቅ አድርጎ መቁጠር የማይታሰብ ነገር ነው!
እስክሞት ድረስ ንጹሕ አቋሜን* አላጎድፍም!*+
6 ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ ደግሞም ፈጽሞ አለቀውም፤+በሕይወት ዘመኔም ሁሉ* ልቤ አይኮንነኝም።*
7 ጠላቴ እንደ ክፉ ሰው ይሁን፤እኔን የሚያጠቁኝ ሰዎች እንደ ዓመፀኛ ይሁኑ።
8 አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው ሲጠፋ፣አምላክ ሕይወቱን* ሲቀጨው ምን ተስፋ ይኖረዋል?+
9 መከራ ሲደርስበትአምላክ ጩኸቱን ይሰማዋል?+
10 ወይስ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ይሰኛል?
ሁልጊዜስ ወደ አምላክ ይጣራል?
11 እኔ ስለ አምላክ ኃይል* አስተምራችኋለሁ፤ሁሉን ቻይ ስለሆነው አምላክ ምንም የምደብቀው ነገር የለም።
12 ሁላችሁም ራእይ ካያችሁ፣ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው?
13 ክፉ ሰው ከአምላክ የሚያገኘው ድርሻ፣+ጨቋኞችም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የሚወርሱት ውርሻ ይህ ነው።
14 ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ዘሮቹም በቂ ምግብ አያገኙም።
15 ከእሱ በኋላ የተረፉት ወገኖቹ በመቅሰፍት ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
16 ብርን እንደ አፈር ቢቆልል፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች እንኳ፣
17 እሱ የሰበሰበውንጻድቁ ሰው ይለብሰዋል፤+ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል።
18 የሚሠራው ቤት ብል እንደሠራው ሽፋን፣ጠባቂም እንደቀለሰው መጠለያ+ በቀላሉ የሚፈርስ ነው።
19 ባለጸጋ ሆኖ ይተኛል፤ ሆኖም ምንም የሚሰበስበው ነገር የለም፤ዓይኑን ሲገልጥ በዚያ ምንም ነገር አይኖርም።
20 ሽብር እንደ ጎርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤አውሎ ነፋስ በሌሊት ይዞት ይሄዳል።+
21 የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እሱም አይገኝም፤ከቦታው ጠርጎ ይወስደዋል።+
22 ከነፋሱ ኃይል ለማምለጥ ሲፍጨረጨር፣+ያለርኅራኄ ተወርውሮ ይመጣበታል።+
23 እጁን ያጨበጭብበታል፤ደግሞም ካለበት ቦታ ሆኖ ያፏጭበታል።*+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “ምሳሌውን።”
^ ወይም “ነፍሴን መራራ ባደረጋት።”
^ ወይም “ከእኔ አላርቅም! እጠብቃለሁ!”
^ ወይም “ስለ የትኛውም ቀኔ።”
^ ወይም “አይዘልፈኝም።”
^ ወይም “ከሃዲ።”
^ ወይም “ነፍሱን።”
^ “በአምላክ እጅ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ “እጃቸውን ያጨበጭቡበታል፤ እንዲሁም ካሉበት ቦታ ሆነው ያፏጩበታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።