ኤርምያስ 1:1-19

  • ኤርምያስ ነቢይ ሆኖ ተሾመ (1-10)

  • የአልሞንድ ዛፍ ራእይ (11, 12)

  • የተጣደው ድስት ራእይ (13-16)

  • ኤርምያስ ተልእኮውን እንዲፈጽም ማበረታቻ ተሰጠው (17-19)

1  በቢንያም አገር በአናቶት+ ከነበሩት ካህናት አንዱ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ* ቃል ይህ ነው። 2  የይሁዳ ንጉሥ የአምዖን+ ልጅ ኢዮስያስ+ በነገሠ በ13ኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 3  ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮዓቄም+ ዘመን፣ እንዲሁም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሴዴቅያስ+ 11ኛው ዓመት የግዛት ዘመን እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ይኸውም ኢየሩሳሌም ወደ ግዞት እስከተወሰደችበት እስከ አምስተኛው ወር+ ድረስ ቃሉ ወደ እሱ መጣ።  4  የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦  5  “በማህፀን ውስጥ ሳልሠራህ በፊት አውቄሃለሁ፤*+ከመወለድህም* በፊት ቀድሼሃለሁ።*+ ለብሔራት ነቢይ አድርጌሃለሁ።”  6  እኔ ግን “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮልኝ! እኔ ገና ልጅ* ስለሆንኩ+ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅም”+ አልኩ።  7  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘እኔ ገና ልጅ ነኝ’ አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ትሄዳለህና፤የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።+  8  ከቁመናቸው የተነሳ አትፍራ፤+‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’+ ይላል ይሖዋ።” 9  ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ።+ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።+ 10  እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”+ 11  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” እኔም “የአልሞንድ ዛፍ* ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩ። 12  ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “በትክክል አይተሃል፤ እኔ ቃሌን ለመፈጸም በከፍተኛ ንቃት እየተጠባበቅኩ ነውና።” 13  የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጥቶ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የተጣደ* ድስት* አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደ ደቡብ ያዘነበለ ነው” አልኩ። 14  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “በምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ላይከሰሜን ጥፋት ይመጣል።+ 15  ‘በሰሜን ያሉትን መንግሥታት ነገዶች ሁሉ እጠራለሁና’ ይላል ይሖዋ፤+‘እነሱም ይመጣሉ፤ እያንዳንዱም ዙፋኑንበኢየሩሳሌም በሮች መግቢያ፣+በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉናበይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያደርጋል።+ 16  ደግሞም እኔን ስለተዉ፣+ለሌሎች አማልክትም የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡና+በገዛ እጃቸው ለሠሯቸው ነገሮች ስለሚሰግዱ+በክፋታቸው ሁሉ ላይ ፍርዴን አውጃለሁ።’ 17  አንተ ግን ለሥራ ተዘጋጅ፤*ደግሞም ተነስ፤ እኔ የማዝህንም ሁሉ ንገራቸው። እኔ ራሴ በፊታቸው እንዳላሸብርህ፣እነሱን አትፍራቸው።+ 18  ምድሪቱን ሁሉ፣ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንቷን፣ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ እንድትቋቋም፣+ዛሬ አንተን የተመሸገ ከተማ፣የብረት ዓምድና የመዳብ ቅጥር አድርጌሃለሁ።+ 19  እነሱም በእርግጥ ይዋጉሃል፤ሆኖም አያሸንፉህም፤*‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’+ ይላል ይሖዋ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ይሖዋ ከፍ ያደርጋል” የሚል ትርጉም ሊኖረው ይችላል።
ቃል በቃል “ከማህፀን ከመውጣትህም በፊት።”
ወይም “ለይቼሃለሁ።”
ወይም “መርጬሃለሁ።”
ወይም “ወጣት።”
ቃል በቃል “ንቁ የሆነው (ዛፍ)።”
ቃል በቃል “እየተራገበ ያለ።”
ወይም “አፉ ሰፊ የሆነ ድስት።”
ቃል በቃል “ዳሌዎችህን ታጠቅ።”
ወይም “ድል አይነሱህም።”