ኤርምያስ 24:1-10

  • ጥሩ በለሶችና መጥፎ በለሶች (1-10)

24  ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+  በአንደኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች በመጀመሪያው ወቅት ላይ እንደሚደርሱ በለሶች ጥሩ ዓይነት ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች ደግሞ መጥፎ ዓይነት ነበሩ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳም ሊበሉ የሚችሉ አልነበሩም።  ከዚያም ይሖዋ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ በለሶች በጣም ጥሩ ዓይነት ናቸው፤ መጥፎዎቹ ደግሞ በጣም መጥፎ ዓይነት ናቸው፤ ከመጥፎነታቸውም የተነሳ ሊበሉ አይችሉም።”+  ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦  “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድኳቸውን የይሁዳ ግዞተኞች እንደነዚህ ጥሩ ዓይነት በለሶች በጥሩ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።  መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ።+ እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።+  እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+  “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+  ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤+ በምበትናቸው ቦታም ሁሉ+ ነቀፋ እንዲደርስባቸው፣ መተረቻ እንዲሆኑ፣ እንዲፌዝባቸውና እንዲረገሙ አደርጋለሁ።+ 10  ለእነሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ሰይፍ፣+ ረሃብና ቸነፈር* እሰዳለሁ።”’”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
ዮአኪን እና ኮንያሁ ተብሎም ይጠራል።
“ምሽግ ከሚገነቡት ሰዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በሽታ።”