ኤርምያስ 47:1-7

  • በፍልስጤማውያን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7)

47  ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን+ በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከሰሜን ውኃ እየመጣ ነው። የሚያጥለቀልቅም ወንዝ ይሆናል። ምድሪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ፣ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል። ሰዎቹ ይጮኻሉ፤በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ።   ከድንጉላ ፈረሶቹ ኃይለኛ የኮቴ ድምፅ፣ከሚንገጫገጩት የጦር ሠረገሎቹ ድምፅናከመንኮራኩሮቹ* የማያባራ ድምፅ የተነሳአባቶች እጃቸው ስለሚዝልልጆቻቸውን ለመርዳት እንኳ ወደ ኋላ አይዞሩም፤   ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና+ ሲዶናን+ የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል። ይሖዋ ፍልስጤማውያንንይኸውም ከካፍቶር*+ ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና።   ጋዛ ትመለጣለች።* አስቀሎን ጸጥ ትላለች።+ ሸለቋሟ በሆነው ሜዳቸው* የምትኖሩ ቀሪዎች ሆይ፣ሰውነታችሁን የምትቆርጡት እስከ መቼ ነው?+   አንተ የይሖዋ ሰይፍ!+ የማታርፈው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ። እረፍ፤ ጸጥ ብለህም ተቀመጥ።   ይሖዋ ትእዛዝ ሰጥቶት እያለእንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል? ትእዛዝ የተሰጠው በአስቀሎንና በባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው፤+በዚያ መድቦታል።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ተሽከርካሪ እግር።
ቀርጤስን ያመለክታል።
በሐዘንና በኀፍረት ራሳቸውን እንደሚላጩ ያመለክታል።
ወይም “ረባዳማ በሆነው ሜዳቸው።”