ኤርምያስ 48:1-47

  • በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-47)

48  የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ሞዓብ+ እንዲህ ይላል፦ “ወዮ፣ ነቦ+ ጠፍታለችና! ቂርያታይም+ ኀፍረት ተከናንባለች፤ ደግሞም ተይዛለች። አስተማማኝ የሆነው መጠጊያ ተዋርዷል፤ ፈራርሷልም።+   ከእንግዲህ ሞዓብን አያወድሷትም። ለውድቀት ትዳረግ ዘንድ፣ ‘ኑ ብሔር መሆኗ እንዲያከትም እንደምስሳት’ ብለው በሃሽቦን+ ይዶልቱባታል። አንቺም ማድመን ሆይ፣ ዝም በይ፤ከኋላሽ ሰይፍ ይከተልሻልና።   ከሆሮናይም+ የጩኸት ድምፅእንዲሁም የጥፋትና የታላቅ ውድቀት ድምፅ ይሰማል።   ሞዓብ ጠፍታለች። ልጆቿ ይጮኻሉ።   ወደ ሉሂት በሚወስደው አቀበት እያለቀሱ ይወጣሉ። በደረሰው ጥፋት የተነሳ፣ ከሆሮናይም ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ሲወርዱም የጭንቅ ጩኸት ይሰማሉ።+   ሽሹ፤ ሕይወታችሁን አትርፉ!* በምድረ በዳ እንዳለ የጥድ ዛፍ ሁኑ።   ምክንያቱም አንቺ በሥራሽና ውድ በሆነ ሀብትሽ ትታመኛለሽ፤ደግሞም ትያዣለሽ። ከሞሽ+ ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋርበአንድነት በግዞት ይወሰዳል።   አጥፊው በእያንዳንዱ ከተማ ላይ ይመጣል፤አንድም ከተማ አያመልጥም።+ ይሖዋ በተናገረው መሠረትሸለቆው* ይጠፋል፤ ደልዳላውም መሬት* እንዳልነበረ ይሆናል።   ለሞዓብ ምልክት አቁሙ፤ስትፈራርስ ትሸሻለችና፤ከተሞቿም አስፈሪ ቦታ ይሆናሉ፤የሚቀመጥባቸውም ሰው አይኖርም።+ 10  ይሖዋ የሰጠውን ተልእኮ በግድየለሽነት የሚያከናውን የተረገመ ነው! ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚመልስ ሰው የተረገመ ነው! 11  ሞዓባውያን ከልጅነታቸው ጀምሮበአምቡላው ላይ እንደረጋ ወይን ጠጅ ተረጋግተው ተቀምጠዋል። ከአንዱ ዕቃ ወደ ሌላው ዕቃ አልተገላበጡም፤በግዞትም ተወስደው አያውቁም። በዚህም ምክንያት ቃናቸው እንዳለ ነው፤መዓዛቸውም አልተለወጠም። 12  “‘ስለዚህ፣ እነሆ እነሱን እንዲገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘እነሱም ይገለብጧቸዋል፤ ዕቃዎቻቸውንም ባዶ ያስቀራሉ፤ ትላልቅ እንስራዎቻቸውንም ይሰባብራሉ። 13  የእስራኤል ቤት ይተማመንበት በነበረው በቤቴል እንዳፈረ ሁሉ ሞዓባውያንም በከሞሽ ያፍራሉ።+ 14  “እኛ ለውጊያ የተዘጋጀን ኃያላን ተዋጊዎች ነን” በማለት እንዴት በድፍረት ትናገራላችሁ?’+ 15  የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ+ እንዲህ ይላል፦‘ሞዓብ ጠፍታለች፤ከተሞቿ ተወረዋል፤+ ምርጥ የሆኑት ወጣቶቻቸውም ታርደዋል።’+ 16  በሞዓባውያን ላይ የሚደርሰው ጥፋት ቀርቧል፤ውድቀታቸውም በፍጥነት እየቀረበ ነው።+ 17  በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ፣ስማቸውን የሚያውቁ ሁሉ አብረዋቸው ያዝናሉ። ‘ኃያሉ በትር፣ የውበትም ዘንግ እንዴት ተሰበረ!’ በሏቸው። 18  አንቺ በዲቦን+ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣ከክብርሽ ውረጂ፤ ተጠምተሽም* ተቀመጪ፤የሞዓብ አጥፊ በአንቺ ላይ መጥቶብሻልና፤የተመሸጉ ቦታዎችሽንም ያፈራርሳል።+ 19  አንቺ በአሮዔር+ የምትኖሪ፣ መንገዱ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ። የሚሸሸውን ወንድና የምታመልጠውን ሴት ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ። 20  ሞዓብ ኀፍረት ተከናነበች፤ በሽብርም ተውጣለች። ዋይ ዋይ በሉ፤ እንዲሁም ጩኹ። ሞዓብ መጥፋቷን በአርኖን+ አውጁ። 21  “ፍርድ ወደ ደልዳላው መሬት* መጥቷል፤+ በሆሎን፣ በያሃጽና+ በመፋአት፣+ 22  በዲቦን፣+ በነቦና+ በቤትዲብላታይም፣ 23  በቂርያታይም፣+ በቤትጋሙልና በቤትምዖን፣+ 24  በቀሪዮትና+ በቦስራ እንዲሁም በሩቅና በቅርብ ባሉ የሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል። 25  ‘የሞዓብ ብርታት* ተቆርጧል፤ክንዱም ተሰብሯል’ ይላል ይሖዋ። 26  ‘በይሖዋ ላይ ስለ ታበየ+ አስክሩት።+ ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤መሳለቂያም ሆኗል። 27  እስራኤል የአንተ መሳለቂያ ሆኖ አልነበረም?+ ራስህን የምትነቀንቀውና እሱን የምትቃወመውእስራኤል ከሌቦች ጋር ተገኝቶ ነው? 28  እናንተ የሞዓብ ነዋሪዎች፣ ከከተሞቹ ወጥታችሁ በቋጥኝ ላይ ኑሩ፤በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ ርግብም ሁኑ።’” 29  “ስለ ሞዓብ ኩራት ሰምተናል፤ እሱ በጣም ትዕቢተኛ ነው፤ስለ እብሪቱ፣ ስለ ኩራቱ፣ ስለ ትዕቢቱና ስለ ልቡ ማበጥ ሰምተናል።”+ 30  “‘ቁጣውን አውቃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ሆኖም ጉራው ከንቱ ይሆናል። አንዳች ነገር አያደርጉም። 31  ከዚህ የተነሳ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ለሞዓብ ምድር ሁሉ እጮኻለሁ፤ለቂርሄረስ+ ነዋሪዎችም እቃትታለሁ። 32  የሲብማ+ ወይን ሆይ፣ ለያዜር+ ከተለቀሰው በበለጠለአንቺ አለቅሳለሁ። የተንዠረገጉት ቅርንጫፎችሽ ባሕሩን ተሻግረዋል። እስከ ባሕሩ፣ እስከ ያዜርም ደርሰዋል። አጥፊው በበጋ ፍሬሽና*ለመከር በደረሰው ወይንሽ ላይ መጥቷል።+ 33  ከፍራፍሬ እርሻውና ከሞዓብ ምድርሐሴትና ደስታ ጠፍቷል።+ ከወይን መጭመቂያዎቹ የወይን ጠጅ መፍሰሱን እንዲያቆም አድርጌአለሁ። በእልልታ ወይን የሚረግጥ ሰው አይኖርም። ጩኸቱ ለየት ያለ ጩኸት ይሆናል።’”+ 34  “‘በሃሽቦን+ የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ኤልዓሌ+ ድረስ ይሰማል። እስከ ያሃጽ+ ድረስ ድምፃቸውን ያሰማሉ፤በዞአር የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ሆሮናይምና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ ድረስ ይሰማል። የኒምሪም ውኃዎች እንኳ ይደርቃሉ።+ 35  ከፍ ባለ የማምለኪያ ቦታ ላይ መባ የሚያቀርበውንናለአምላኩ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰውከሞዓብ አጠፋለሁ’ ይላል ይሖዋ። 36  ‘ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል፤*+ለቂርሄረስ ሰዎችም ልቤ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል።* ያከማቸው ሀብት ይጠፋልና። 37  ራስ ሁሉ ተመልጧል፤+ጢምም ሁሉ ተላጭቷል። እጅ ሁሉ ተሸንትሯል፤+በወገባቸውም ላይ ማቅ ታጥቀዋል!’”+ 38  “‘በሞዓብ ጣሪያዎች ሁሉናበአደባባዮቿ ሁሉ ላይከዋይታ ሌላ የሚሰማ ነገር የለም። ሞዓብን እንደተጣለ እንስራሰባብሬአታለሁና’ ይላል ይሖዋ። 39  ‘እጅግ ተሸብራለች! ዋይ ዋይ በሉ! ሞዓብ ኀፍረት ተከናንቦ ጀርባውን አዙሯል! ሞዓብ መሳለቂያ ሆኗል፤በዙሪያው ያሉት ሁሉ ከእሱ የተነሳ ይደነግጣሉ።’” 40  “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ተወንጭፎ እንደሚወርድ ንስር፣+እሱም በሞዓብ ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።+ 41  ከተሞቹ ይወረራሉ፤ምሽጎቿም ይያዛሉ። በዚያ ቀን የሞዓብ ተዋጊዎች ልብምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።’” 42  “‘ሞዓብም ሕዝብ መሆኑ ያከትማል፤+በይሖዋ ላይ ታብዮአልና።+ 43  የሞዓብ ነዋሪ ሆይ፣ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል’ ይላል ይሖዋ። 44  ‘ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓዱ ውስጥ ይወድቃል፤ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።’ ‘የሚቀጡበትን ዓመት በሞዓብ ላይ አመጣለሁና’ ይላል ይሖዋ። 45  ‘የሚሸሹት ሰዎች ኃይላቸው ተሟጦ በሃሽቦን ጥላ ሥር ይቆማሉ። ከሃሽቦን እሳት፣ከሲሖን መካከልም ነበልባል ይወጣልና።+ የሞዓብን ግንባርናየሁከት ልጆችን ራስ ቅል ይበላል።’+ 46  ‘ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! የከሞሽ+ ሰዎች ጠፍተዋል። ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፤ሴቶች ልጆችህም በግዞት ተወስደዋል።+ 47  በዘመኑ መጨረሻ ግን፣ ከሞዓብ የተማረኩትን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በሞዓብ ላይ የተላለፈው የፍርድ መልእክት እዚህ ላይ ይደመደማል።’”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሳችሁን አትርፉ!”
ወይም “ረባዳማው ሜዳ።”
ወይም “አምባውም።”
“በደረቅ መሬትም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ወደ አምባው።”
ቃል በቃል “ቀንድ።”
የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።
ወይም “ይጮኻል።”
በቀብር ጊዜ ሐዘናቸውን ለመግለጽ የሚጫወቱትን ዋሽንት ያመለክታል።
ወይም “ይጮኻል።”
በቀብር ጊዜ ሐዘናቸውን ለመግለጽ የሚጫወቱትን ዋሽንት ያመለክታል።