ኤርምያስ 5:1-31
5 በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ።
ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ።
ፍትሕን የሚያደርግ፣+ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነበአደባባዮቿ ፈልጉ፤እኔም ይቅር እላታለሁ።
2 “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም
የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው።+
3 ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም?+
አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም።*
አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም።+
ፊታቸውን ከዓለት ይልቅ አጠነከሩ፤+ለመመለስም አሻፈረን አሉ።+
4 እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው።
የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸውየሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።
5 ታዋቂ ወደሆኑት ሰዎች ሄጄ አነጋግራቸዋለሁ፤እነሱ የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድአስተውለው መሆን አለበትና።+
ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤ማሰሪያውንም በጥሰዋል።”
6 ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል።
ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል።
በደላቸው በዝቷልና፤የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል።+
7 ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ?
ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ።+
እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ።
8 እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል።+
9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።
“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?”+
10 “የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት።+
የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤የይሖዋ አይደሉምና።
11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤትበእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ።+
12 “እነሱ ይሖዋን ክደዋል፤‘እሱ ምንም ነገር አያደርግም።*+
በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ።+
13 ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤ቃሉም* በውስጣቸው የለም።
ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!”
14 ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነዚህ ሰዎች እንዲህ ስለሚሉ፣ቃሌን በአፋችሁ ውስጥ እሳት አደርጋለሁ፤+እንጨቱ ደግሞ ይህ ሕዝብ ነው፤እሳቱም ይበላቸዋል።”+
15 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።
“እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው።
ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣ቋንቋውን የማታውቀውናንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው።+
16 የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው።
17 እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ።
መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ።
የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ።
የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።”
18 “ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም።+
19 ‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።”+
20 ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦
21 “እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች* ይህን ስሙ፦+
ዓይን አላቸው ግን አያዩም፤+ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም።+
22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም?
ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌአሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ።
ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+
23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል።+
24 እነሱም በልባቸው
“እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብበወቅቱ የሚሰጠንን፣የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንንአምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም።+
25 የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል።+
26 በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና።
አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ።
ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ።
ሰዎችን ያጠምዳሉ።
27 በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው።+
ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው።
28 ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤በክፋት ተሞልተዋል።
ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡአባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤+ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’”+
29 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።
“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?
30 በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦
31 ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ።
የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+
ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?”
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “እነሱ ግን አልደከሙም።”
^ ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”
^ “እሱ የለም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ የአምላክን ቃል ያመለክታል።
^ ቃል በቃል “ልብ የሚጎድላችሁ ሞኞች።”
^ ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”