ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ 2:1-18
2 ቀስ በቀስ እንዳንወሰድ+ ለሰማናቸው ነገሮች ከወትሮው የበለጠ ትኩረት መስጠታችን አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።+
2 በመላእክት አማካኝነት የተነገረው ቃል+ የጸና መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲሁም ማንኛውም አለመታዘዝና መተላለፍ ከፍትሕ ጋር የሚስማማ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ+
3 እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንል እንዴት ከቅጣት ልናመልጥ እንችላለን?+ ይህ መዳን መጀመሪያ ጌታችን የተናገረው+ ሲሆን እሱን የሰሙት ሰዎችም ለእኛ አረጋግጠውልናል፤
4 አምላክም በምልክቶች፣ በድንቅ ነገሮች፣ በተለያዩ ተአምራትና+ ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማደል መሥክሯል።+
5 ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም+ያስገዛው ለመላእክት አይደለምና።
6 ነገር ግን አንድ ምሥክር፣ አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ወይስ ትንከባከበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?+
7 ከመላእክት ጥቂት አሳነስከው፤ የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፋህለት፤ እንዲሁም በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምከው።
8 ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛህለት።”+ አምላክ ሁሉንም ነገር ለእሱ ስላስገዛ፣+ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም።+ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም።+
9 ነገር ግን ከመላእክት በጥቂቱ እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ+ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ+ አሁን የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል።+
10 ሁሉ ነገር የሚኖረው ለአምላክ ነው፤ የሚኖረውም በእሱ አማካኝነት ነው። ስለዚህ አምላክ ብዙ ልጆችን ክብር ለማጎናጸፍ+ ሲል ለመዳን የሚያበቃቸውን “ዋና ወኪል”+ በመከራ አማካኝነት ፍጹም ማድረጉ የተገባ ነበር።+
11 የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሰዎች፣+ ሁሉም ከአንድ አባት የመጡ ናቸውና፤+ ከዚህም የተነሳ እነሱን ወንድሞች ብሎ ለመጥራት አያፍርም፤+
12 ምክንያቱም “ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤ በጉባኤ መካከልም በመዝሙር አወድስሃለሁ” ይላል።+
13 ደግሞም “እኔ እምነቴን በእሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል።+ እንደገናም “እነሆ! እኔና ይሖዋ* የሰጠኝ ልጆች” ይላል።+
14 ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤+ ይህም የሆነው ለሞት የመዳረግ አቅም ያለውን+ ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤+
15 እንዲሁም ሞትን በመፍራታቸው በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ በባርነት ቀንበር የተያዙትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ ነው።+
16 እሱ እየረዳ ያለው መላእክትን እንዳልሆነ የታወቀ ነውና፤ ከዚህ ይልቅ እየረዳ ያለው የአብርሃምን ዘር ነው።+
17 ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ*+ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ እንደ “ወንድሞቹ” መሆን አስፈለገው።+
18 በተፈተነ ጊዜ እሱ ራሱ መከራ ስለደረሰበት+ በፈተና ላይ ላሉት ሊደርስላቸው ይችላል።+