ዘካርያስ 3:1-10
3 እሱም ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን+ በይሖዋ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፤ ሰይጣንም+ እሱን ለመቃወም በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።
2 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤+ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው+ ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?”
3 ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር።
4 መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን “ያደፈውን ልብሱን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም እሱን “እነሆ፣ ጥፋትህን* አስወግጄልሃለሁ፤ ደግሞም ጥሩ ልብስ ትለብሳለህ”*+ አለው።
5 እኔም “በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም ይደረግለት”+ አልኩ። እነሱም ንጹሑን ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት፤ የይሖዋም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።
6 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ኢያሱን እንዲህ አለው፦
7 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመንገዶቼ ብትመላለስና በፊቴ ኃላፊነቶችህን ብትወጣ፣ በቤቴ ፈራጅ ሆነህ ታገለግላለህ፤+ ቅጥር ግቢዎቼንም ትንከባከባለህ፤* እኔም እዚህ በቆሙት መካከል በነፃነት የመቅረብ መብት እሰጥሃለሁ።’
8 “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ+ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!+
9 በኢያሱ ፊት ያስቀመጥኩትን ድንጋይ እዩ! በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፤ እኔም በላዩ ላይ ጽሑፍ እቀርጻለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።’+
10 “‘በዚያ ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘እያንዳንዳችሁ ጎረቤታችሁን ከወይናችሁና ከበለስ ዛፋችሁ ሥር እንዲቀመጥ ትጋብዛላችሁ።’”+