ዘፍጥረት 36:1-43
36 የኤሳው ማለትም የኤዶም + ታሪክ ይህ ነው።
2 ኤሳው ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ እነሱም የሂታዊው+ የኤሎን ልጅ አዳ+ እንዲሁም የአና ልጅና የሂዋዊው የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው ኦሆሊባማ+ ናቸው፤
3 በተጨማሪም የእስማኤል ልጅ የሆነችውን የነባዮትን+ እህት ባሴማትን+ አገባ።
4 አዳ ለኤሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማት ደግሞ ረኡዔልን ወለደች፤
5 ኦሆሊባማ የኡሽን፣ ያላምን እና ቆሬን ወለደች።+
እነዚህ ኤሳው በከነአን ምድር ሳለ የተወለዱለት ልጆች ናቸው።
6 ከዚያም ኤሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ የቤተሰቡን አባላት* ሁሉ፣ መንጋውን፣ ሌሎቹን እንስሳት ሁሉና በከነአን ምድር ያፈራውን ሀብት ሁሉ+ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ርቆ ወደ ሌላ ምድር ሄደ።+
7 ምክንያቱም ንብረታቸው በጣም ስለበዛ አብረው መኖር አልቻሉም፤ እንዲሁም ከመንጋቸው ብዛት የተነሳ ይኖሩበት* የነበረው ምድር ሊበቃቸው አልቻለም።
8 በመሆኑም ኤሳው በሴይር ተራራማ አካባቢ መኖር ጀመረ።+ ኤሳው ኤዶም ተብሎም ይጠራል።+
9 በሴይር ተራራማ አካባቢ የሚኖረው የኤዶማውያን አባት የኤሳው ታሪክ ይህ ነው።+
10 የኤሳው ወንዶች ልጆች ስም የሚከተለው ነው፦ የኤሳው ሚስት የአዳ ልጅ ኤሊፋዝና የኤሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረኡዔል ናቸው።+
11 የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ቴማን፣+ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም እና ቀናዝ+ ናቸው።
12 ቲምና የኤሳው ልጅ የኤሊፋዝ ቁባት ሆነች። ከጊዜ በኋላም ለኤሊፋዝ አማሌቅን+ ወለደችለት። የኤሳው ሚስት የአዳ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው።
13 የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ ናቸው። እነዚህም የኤሳው ሚስት የባሴማት+ ልጆች ነበሩ።
14 የአና ልጅና የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለኤሳው የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ ናቸው።
15 የነገድ አለቆች* የሆኑት የኤሳው ወንዶች ልጆች+ የሚከተሉት ናቸው፦ የኤሳው የበኩር ልጅ የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆችም አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ጸፎ፣ አለቃ ቀናዝ፣+
16 አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጋታም እና አለቃ አማሌቅ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የኤሊፋዝ ልጆች+ ነበሩ። እነዚህ የአዳ ወንዶች ልጆች ናቸው።
17 የኤሳው ልጅ የረኡዔል ወንዶች ልጆች፣ አለቃ ናሃት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሻማህ እና አለቃ ሚዛህ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የረኡዔል ልጆች+ ናቸው። እነዚህ የኤሳው ሚስት የባሴማት ወንዶች ልጆች ናቸው።
18 በመጨረሻም የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ወንዶች ልጆች፣ አለቃ የኡሽ፣ አለቃ ያላም እና አለቃ ቆሬ ናቸው። እነዚህ የነገድ አለቆች የአና ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች ናቸው።
19 የኤሳው ማለትም የኤዶም+ ወንዶች ልጆችና አለቆቻቸው እነዚህ ናቸው።
20 በዚያ ምድር የሚኖሩት የሆራዊው የሴይር ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦+ ሎጣን፣ ሾባል፣ ጺብኦን፣ አና፣+
21 ዲሾን፣ ኤጼር እና ዲሻን።+ እነዚህ በኤዶም ምድር የሆራውያን የነገድ አለቆች የሆኑት የሴይር ወንዶች ልጆች ናቸው።
22 የሎጣን ወንዶች ልጆች ሆሪ እና ሄማም ናቸው፤ የሎጣን እህት ቲምና ትባላለች።+
23 የሾባል ወንዶች ልጆች አልዋን፣ ማናሃት፣ ኤባል፣ ሼፎ እና ኦናም ናቸው።
24 የጺብኦን+ ወንዶች ልጆች አያ እና አና ናቸው። ይህ አና የአባቱን የጺብኦንን አህዮች ሲጠብቅ በምድረ በዳ የፍል ውኃ ምንጮችን ያገኘው ነው።
25 የአና ልጆች ዲሾን እና የአና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ ናቸው።
26 የዲሾን ወንዶች ልጆች ሄምዳን፣ ኤሽባን፣ ይትራን እና ኬራን ናቸው።+
27 የኤጼር ወንዶች ልጆች ቢልሃን፣ ዛአዋን እና አቃን ናቸው።
28 የዲሻን ወንዶች ልጆች ዑጽ እና አራን ናቸው።+
29 የሆራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ናቸው፦ አለቃ ሎጣን፣ አለቃ ሾባል፣ አለቃ ጺብኦን፣ አለቃ አና፣
30 አለቃ ዲሾን፣ አለቃ ኤጼር እና አለቃ ዲሻን።+ በሴይር ምድር የሆራውያን የነገድ አለቆች በየአለቆቻቸው ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው።
31 እነዚህ በእስራኤላውያን* ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት+ በኤዶም ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው።+
32 የቢዖር ልጅ ቤላ በኤዶም ይገዛ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
33 ቤላ ሲሞት የቦስራው የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ።
34 ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ።
35 ሁሻም ሲሞት ምድያማውያንን+ በሞዓብ ክልል* ድል ያደረጋቸው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ፤ የከተማውም ስም አዊት ይባል ነበር።
36 ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ።
37 ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ።
38 ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ።
39 የአክቦር ልጅ ባአልሀናን ሲሞት ሃዳር በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት።
40 እንግዲህ የኤሳው ልጆች የሆኑ የነገድ አለቆች በየቤተሰባቸው፣ በየስፍራቸውና በየስማቸው ሲዘረዘሩ ስማቸው ይህ ነው፦ አለቃ ቲምና፣ አለቃ አልዋህ፣ አለቃ የቴት፣+
41 አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላህ፣ አለቃ ፒኖን፣
42 አለቃ ቀናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣
43 አለቃ ማግዲኤል እና አለቃ ኢራም። ከኤዶም የተገኙት የነገድ አለቆች ርስት አድርገው በያዙት ምድር እንደየመኖሪያቸው ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው።+ የኤዶማውያን አባት ኤሳው ይህ ነው።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “በቤቱ ውስጥ ያለውን ነፍስ።”
^ ወይም “እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነው ይኖሩበት።”
^ ቃል በቃል “ሺኮች።” የነገድ አለቃ የሆነ ሰው “ሺክ” ተብሎ ይጠራ ነበር።
^ ቃል በቃል “በእስራኤል ወንዶች ልጆች።”
^ ቃል በቃል “ሜዳ።”