የዮሐንስ የመጀመሪያው ደብዳቤ 4:1-21
4 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ በመንፈስ የተነገረን ቃል* ሁሉ አትመኑ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ የተነገሩት ቃላት* ከአምላክ የመነጩ መሆን አለመሆናቸውን መርምሩ፤+ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+
2 በመንፈስ የተነገረው ቃል ከአምላክ የመነጨ መሆኑን በዚህ ማወቅ ትችላላችሁ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚመሠክር በመንፈስ የተነገረ ቃል ሁሉ ከአምላክ የመነጨ ነው።+
3 ሆኖም ስለ ኢየሱስ የማይመሠክር በመንፈስ የተነገረ ቃል ሁሉ ከአምላክ የሚመነጭ አይደለም።+ ይህ በመንፈስ የተነገረ ቃል ከፀረ ክርስቶስ የሚመነጭ ነው፤ ፀረ ክርስቶስ እንዲህ ያሉ ነገሮችን እንደሚናገር ሰምታችኋል፤+ አሁንም እንኳ ይህ ቃል በዓለም ላይ እየተነገረ ነው።+
4 ልጆቼ ሆይ፣ እናንተ ከአምላክ ወገን ናችሁ፤ እነሱንም* አሸንፋችኋል፤+ ምክንያቱም ከእናንተ ጎን ያለው፣+ ከዓለም ጎን ካለው ይበልጣል።+
5 እነሱ የዓለም ወገን ናቸው፤+ ከዓለም የሚመነጨውን ነገር የሚናገሩትና ዓለምም የሚሰማቸው ለዚህ ነው።+
6 እኛ ከአምላክ ወገን ነን። አምላክን የሚያውቅ ሁሉ ይሰማናል፤+ ከአምላክ ወገን ያልሆነ ሁሉ አይሰማንም።+ በመንፈስ የተነገረውን የእውነት ቃልና በመንፈስ የተነገረውን የስህተት ቃል ለይተን የምናውቀው በዚህ መንገድ ነው።+
7 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እርስ በርስ መዋደዳችንን እንቀጥል፤+ ምክንያቱም ፍቅር ከአምላክ ነው፤ ፍቅር የሚያሳይ ሁሉ ከአምላክ የተወለደ ሲሆን አምላክን ያውቃል።+
8 ፍቅር የማያሳይ አምላክን አያውቅም፤ ምክንያቱም አምላክ ፍቅር ነው።+
9 የአምላክ ፍቅር ከእኛ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዚህ መንገድ ተገልጧል፤ እኛ በእሱ አማካኝነት ሕይወት ማግኘት እንድንችል+ አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታል።+
10 ይህ ፍቅር የተገለጠው በዚህ መንገድ ነው፦ እኛ አምላክን ስለወደድነው ሳይሆን እሱ ስለወደደንና ለኃጢአታችን የማስተሰረያ መሥዋዕት* እንዲሆን+ ልጁን ስለላከ ነው።+
11 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ አምላክ የወደደን በዚህ መንገድ ከሆነ እኛም እርስ በርሳችን የመዋደድ ግዴታ አለብን።+
12 መቼም ቢሆን አምላክን ያየው ማንም የለም።+ እርስ በርስ መዋደዳችንን ከቀጠልን አምላክ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ ፍቅሩም በመካከላችን ፍጹም ይሆናል።+
13 እሱ መንፈሱን ስለሰጠን እኛ ከእሱ ጋር አንድነት እንዳለንና እሱም ከእኛ ጋር አንድነት እንዳለው እናውቃለን።
14 ከዚህ በተጨማሪ አብ ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጎ እንደላከው እኛ ራሳችን አይተናል፤ ደግሞም እየመሠከርን ነው።+
15 ማንም ሰው ኢየሱስ የአምላክ ልጅ መሆኑን የሚመሠክር+ ከሆነ አምላክ እንዲህ ካለው ሰው ጋር አንድነት ይኖረዋል፤ እሱም ከአምላክ ጋር አንድነት ይኖረዋል።+
16 ደግሞም አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል፤ እንዲሁም አምነናል።+
አምላክ ፍቅር ነው፤+ በፍቅር የሚኖር ከአምላክ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ይኖራል፤ አምላክም ከእሱ ጋር አንድነት ይኖረዋል።+
17 በመሆኑም በፍርድ ቀን የመናገር ነፃነት* ይኖረን ዘንድ+ ፍቅር በእኛ መካከል ፍጹም የሆነው በዚህ መንገድ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ ዓለም ውስጥ እኛ ራሳችን እንደ እሱ* ነን።
18 በፍቅር ፍርሃት የለም፤+ እንዲያውም ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤* ምክንያቱም ፍርሃት ወደኋላ እንድንል ያደርገናል። ደግሞም የሚፈራ ሰው ፍጹም የሆነ ፍቅር የለውም።+
19 እሱ አስቀድሞ ስለወደደን እኛም ፍቅር እናሳያለን።+
20 ማንም “አምላክን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን የሚጠላ ከሆነ ይህ ሰው ውሸታም ነው።+ ያየውን ወንድሙን የማይወድ+ ያላየውን አምላክ ሊወድ አይችልምና።+
21 እሱም “አምላክን የሚወድ ሁሉ ወንድሙንም መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥቶናል።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “መናፍስት።”
^ ቃል በቃል “መንፈስን።”
^ ይህ ቃል ሐሰተኛ ነቢያትን ያመለክታል።
^ ወይም “የእርቅ መሥዋዕት።”
^ ወይም “የመተማመን ስሜት።”
^ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለክታል።
^ ወይም “ያስወግዳል።”