ለጢሞቴዎስ የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 1:1-20
1 አዳኛችን በሆነው አምላክና ተስፋችን+ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣
2 በእምነት እውነተኛ ልጄ+ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፦*+
አባት ከሆነው አምላክና ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን።
3 ወደ መቄዶንያ ልሄድ በተነሳሁበት ጊዜ በኤፌሶን እንድትቆይ እንዳበረታታሁህ ሁሉ አሁንም አንዳንዶች የሐሰት ትምህርት እንዳያስፋፉ ታዛቸው ዘንድ በዚያው እንድትቆይ አበረታታሃለሁ፤
4 በተጨማሪም ለፈጠራ ወሬዎችና+ ለትውልድ ሐረግ ቆጠራ ትኩረት እንዳይሰጡ እዘዛቸው። እንዲህ ያሉ ነገሮች ለግምታዊ ሐሳቦች በር ከመክፈት ውጭ የሚያስገኙት ፋይዳ የለም፤+ አምላክ እምነትን ለማጠናከር ከሚሰጠው ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።
5 የዚህ ትእዛዝ* ዓላማ ከንጹሕ ልብ፣ ከጥሩ ሕሊናና ግብዝነት ከሌለበት እምነት+ የሚመነጭ ፍቅር+ እንዲኖረን ነው።
6 አንዳንዶች እነዚህን ነገሮች በመተው ፍሬ ቢስ ወደሆነ ወሬ ፊታቸውን አዙረዋል።+
7 የሕግ አስተማሪዎች+ መሆን ይፈልጋሉ፤ ሆኖም የሚናገሯቸውን ነገሮችም ሆነ አጥብቀው የሚሟገቱላቸውን ነገሮች አያስተውሉም።
8 አንድ ሰው በአግባቡ ሥራ ላይ እስካዋለው ድረስ ሕጉ መልካም ነው፤
9 ደግሞም ሕግ የሚወጣው ለጻድቅ ሰው ሳይሆን ሕግ ለሚተላለፉና+ ለዓመፀኞች፣ ፈሪሃ አምላክ ለሌላቸውና ለኃጢአተኞች፣ ታማኞች ላልሆኑና* ቅዱስ የሆነውን ለሚንቁ፣ አባትንና እናትን ለሚገድሉ እንዲሁም ለነፍሰ ገዳዮች መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል፤
10 በተጨማሪም ለሴሰኞች፣* ግብረ ሰዶም ለሚፈጽሙ ወንዶች፣* ለአፋኞች፣ ለውሸታሞችና በሐሰት ለሚምሉ* እንዲሁም ትክክለኛውን* ትምህርት+ ለሚጻረሩ ነገሮች ሁሉ ነው፤
11 ይህ ትምህርት ደስተኛው አምላክ ከገለጸው ክብራማ ምሥራች ጋር የሚስማማ ሲሆን እሱም ምሥራቹን በአደራ ሰጥቶኛል።+
12 ለአገልግሎቱ በመሾም ታማኝ አድርጎ ስለቆጠረኝ ኃይል የሰጠኝን ጌታችን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ፤+
13 ምንም እንኳ ቀደም ሲል አምላክን የምሳደብ፣ አሳዳጅና እብሪተኛ የነበርኩ ብሆንም ይህን አድርጎልኛል።+ ደግሞም ባለማወቅና ባለማመን ስላደረግኩት፣ ምሕረት ተደርጎልኛል።
14 የጌታችን ጸጋም ከእምነት እንዲሁም የክርስቶስ ኢየሱስ ተከታይ በመሆኔ ምክንያት ካገኘሁት ፍቅር ጋር እጅግ ተትረፍርፎልኛል።
15 ‘ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን+ ወደ ዓለም መጣ’ የሚለው ቃል እምነት የሚጣልበትና ሙሉ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚገባው ነው። ከኃጢአተኞች ደግሞ እኔ ዋነኛ ነኝ።+
16 ይሁንና ለእኔ ምሕረት የተደረገው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ዋነኛ ኃጢአተኛ የሆንኩትን እኔን ምሳሌ አድርጎ በመጠቀም የዘላለም ሕይወት ለማግኘት እምነታቸውን በእሱ ላይ ለሚጥሉ ሰዎች ትዕግሥቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ነው።+
17 እንግዲህ ለማይጠፋውና+ ለማይታየው፣+ እሱ ብቻ አምላክ ለሆነው+ ለዘላለሙ ንጉሥ+ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን። አሜን።
18 ልጄ ጢሞቴዎስ፣ ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በተነገሩት ትንቢቶች መሠረት ይህን ትእዛዝ* በአደራ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም ከእነዚህ ጋር በሚስማማ መንገድ መልካሙን ውጊያ መዋጋትህን እንድትቀጥል ነው፤+
19 ይህን የምታደርገው እምነትንና ጥሩ ሕሊናን+ አጥብቀህ በመያዝ ነው፤ አንዳንዶች ሕሊናቸውን ወደ ጎን ገሸሽ በማድረጋቸው ባሕር ላይ አደጋ ደርሶበት እንደተሰባበረ መርከብ እምነታቸው ጠፍቷል።
20 ከእነሱም መካከል ሄሜኔዎስና+ እስክንድር ይገኙበታል፤ እነሱ ከተግሣጽ ተምረው በአምላክ ላይ የስድብ ቃል ከመናገር እንዲቆጠቡ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁ።*+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ “አምላክን የሚያከብር ሰው” የሚል ትርጉም አለው።
^ ወይም “መመሪያ።”
^ ወይም “ታማኝ ፍቅር ለሌላቸውና።”
^ ወይም “መሐላ ለሚያፈርሱ።”
^ ወይም “ጤናማውን፤ ጠቃሚውን።”
^ የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
^ ወይም “ከወንዶች ጋር የፆታ ግንኙነት ለሚፈጽሙ ወንዶች።” ቃል በቃል “ከወንዶች ጋር ለሚተኙ ወንዶች።”
^ ወይም “መመሪያ።”
^ ከጉባኤ መወገዳቸውን ያመለክታል።