የጴጥሮስ የመጀመሪያው ደብዳቤ 5:1-14
5 ስለዚህ እኔም እንደ እነሱ ሽማግሌ እንዲሁም የክርስቶስ መከራ ምሥክርና ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ እንደመሆኔ መጠን+ በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እንዲህ በማለት አጥብቄ እለምናለሁ፦*
2 የበላይ ተመልካቾች ሆናችሁ በማገልገል* በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክን መንጋ እንደ እረኞች ሆናችሁ ተንከባከቡ፤+ ሥራችሁን በግዴታ ሳይሆን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ተወጡ፤+ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን+ ለማገልገል በመጓጓት፣
3 የአምላክ ንብረት በሆኑት ላይ ሥልጣናችሁን በማሳየት ሳይሆን+ ለመንጋው ምሳሌ በመሆን ጠብቁ።+
4 የእረኞች አለቃ+ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋ የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።+
5 በተመሳሳይም እናንተ ወጣቶች፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ።+ ይሁንና እርስ በርስ ባላችሁ ግንኙነት ሁላችሁም ትሕትናን ልበሱ፤* ምክንያቱም አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።+
6 ስለዚህ በተገቢው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው የአምላክ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤+
7 የሚያስጨንቃችሁንም* ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤+ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።+
8 የማስተዋል ስሜታችሁን ጠብቁ፤ ንቁ ሆናችሁ ኑሩ!+ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል።+
9 ሆኖም በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉት ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንዳለ ተገንዝባችሁ+ በእምነት ጸንታችሁ በመቆም ተቃወሙት።+
10 ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ አንድነት ወደ ዘላለማዊ ክብሩ የጠራችሁ+ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እሱ ራሱ ሥልጠናችሁ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል። ጽኑ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፤+ ደግሞም ያጠነክራችኋል፤+ አጽንቶም ያቆማችኋል።
11 ኃይል ለዘላለም የእሱ ይሁን። አሜን።
12 እኔ ታማኝ ወንድም አድርጌ በምቆጥረው በስልዋኖስ*+ አማካኝነት ይህን በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍኩላችሁም እናንተን ለማበረታታትና ይህ የአምላክ እውነተኛ ጸጋ እንደሆነ አጥብቄ ለመመሥከር ነው። ይህን ጸጋ አጥብቃችሁ ያዙ።
13 እንደ እናንተ የተመረጠችው በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ ልጄ ማርቆስም+ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።
14 በፍቅር እርስ በርስ በመሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ።
ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያላችሁ ሁሉ፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “እመክራለሁ።”
^ ወይም “መንጋውን በጥንቃቄ በመከታተል።”
^ ወይም “ታጠቁ።”
^ ወይም “የሚያሳስባችሁንም።”
^ ሲላስ ተብሎም ይጠራል።