በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣ

3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

“ጥሩ የሆነውን፣ ተቀባይነት ያለውንና ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መርምራችሁ ማረጋገጥ ትችሉ ዘንድ አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ።”ሮም 12:2

ምን ማለት ነው?

አምላክ የምናስብበት መንገድ ያሳስበዋል። (ኤርምያስ 17:10) ጥላቻ የሚንጸባረቅበት ነገር መናገር ወይም ማድረግ እንደሌለብን ግልጽ ነው፤ ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም። የጥላቻ ሰንሰለት የሚጀምረው በአእምሮና በልብ ውስጥ ነው። ስለዚህ ጥላቻን ከአስተሳሰባችንም ሆነ ከስሜታችን ነቅለን ማውጣት ይኖርብናል። እውነተኛ ‘ለውጥ’ ማድረግና የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የምንችለው እንዲህ ካደረግን ብቻ ነው።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ስለ ሌሎች፣ በተለይም ሌላ ዘር ወይም ዜግነት ስላላቸው ሰዎች ያለህን አመለካከትና ስሜት በሐቀኝነት መርምር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ስለ እነሱ ምን አመለካከት አለኝ? አመለካከቴ የተመሠረተው ስለ እነሱ በትክክል በማውቀው ነገር ላይ ነው? ወይስ በብዙኃኑ አመለካከት ላይ?’ ጥላቻንና ዓመፅን ከሚያንጸባርቁ ማኅበራዊ ሚዲያዎች፣ ፊልሞችና መዝናኛዎች ራቅ።

የአምላክ ቃል ጥላቻን ከልባችንና ከአእምሯችን ለማስወገድ ይረዳናል

የራሳችንን አስተሳሰብና ስሜት ሚዛናዊ ሆነን መገምገም ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ሆኖም የአምላክ ቃል ‘የልባችንን ሐሳብና ዓላማ ለመረዳት’ ያስችለናል። (ዕብራውያን 4:12) ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህን ቀጥል። አስተሳሰብህን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች አንጻር ገምግም፤ እንዲሁም አስተሳሰብህን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ጋር ለማስማማት የቻልከውን ሁሉ ጥረት አድርግ። የአምላክ ቃል በአእምሯችንና በልባችን ውስጥ ‘የተመሸገውን’ ጥላቻ ለማስወገድ ይረዳናል።—2 ቆሮንቶስ 10:4, 5