በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2023 | የአእምሮ ጤንነት—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው እርዳታ

በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የአእምሮ ጤና መቃወስ ያጋጥማቸዋል። የተለያየ ዕድሜ፣ የኑሮ ደረጃ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ዘር እና ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች ከስሜት ቀውስ ጋር ይታገላሉ። ለመሆኑ የአእምሮ ሕመም ምንድን ነው? በሰዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረውስ እንዴት ነው? ይህ መጽሔት፣ ተገቢውን የሕክምና እርዳታ ማግኘት ስላለው ጥቅም እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ ችግር ላጋጠማቸው ሰዎች ስለሚሰጠው እርዳታ ያብራራል።

 

ዓለም አቀፍ የአእምሮ ጤና ቀውስ

ማንም ሰው በአእምሮ ሕመም ሊጠቃ ይችላል። የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ለአእምሮ ጤንነትህ የሚጠቅምህ እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

አምላክ ያስብልሃል

ይሖዋ አምላክ ከማንም በተሻለ ሐሳብህንና ስሜትህን እንደሚረዳልህ መተማመን የምትችለው ለምንድን ነው?

1 | ጸሎት—‘የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ’

ስለሚያሳስብህ ወይም ስለሚያስጨንቅህ ስለ ማንኛውም ነገር ወደ አምላክ መጸለይ ትችላለህ? በጭንቀት የሚሠቃዩ ሰዎችን ጸሎት የሚረዳቸው እንዴት ነው?

2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’

መጽሐፍ ቅዱስ በቅርቡ የስሜት ሥቃይ ያለፈ ታሪክ እንደሚሆን የሚገልጽ ተስፋ ይሰጠናል።

3 | ከመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች የምናገኘው ትምህርት

እንደ እኛው ዓይነት ስሜት ስለነበራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ማንበባችን ከስሜት ሥቃይ ጋር የምንታገለው እኛ ብቻ እንዳልሆንን እንዲሰማን ያደርጋል።

4 | መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ ማሰላሰልና ምክንያታዊ ግብ ማውጣት የአእምሮ ጤንነትህን ለማሻሻል የሚረዳህ እንዴት ነው?

ከአእምሮ ጤንነት መቃወስ ጋር የሚታገሉ ሰዎችን መርዳት

የአእምሮ ጤንነት መቃወስ ያጋጠመውን ጓደኛህን መርዳትህ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።