በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?

የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?

ሞት ያላንኳኳው በር የለም። ይሁንና ሞት የሁሉም ነገር መጨረሻ ነው? የሞቱ ሰዎች ተረስተው ይቀራሉ? ወይስ ተስፋ አላቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሙታን አይረሱም

“በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ . . . ይወጣሉ።”—ዮሐንስ 5:28, 29

አምላክ የሞቱ ሰዎችን አስታውሶ ከሞት ያስነሳቸዋል።

በምድር ላይ ትንሣኤ ይኖራል

“ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች ከሞት [ይነሳሉ]።”—የሐዋርያት ሥራ 24:15

በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት ይነሳሉ፤ ለዘላለም በሰላም የመኖር ተስፋም ይኖራቸዋል።

የትንሣኤ ተስፋ አስተማማኝ ነው

“[አምላክ] የከዋክብትን ብዛት ይቆጥራል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።”—መዝሙር 147:4

አምላክ ሁሉንም ከዋክብት በየስማቸው መጥራት ከቻለ ከሞት የሚያስነሳቸውን ሰዎች ማስታወስ ለእሱ ቀላል ነው።