መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መስከረም 2016
ይህ እትም ከጥቅምት 24 እስከ ኅዳር 27, 2016 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
‘እጆቻችሁ አይዛሉ’
ይሖዋ አገልጋዮቹን የሚያጠነክረውና የሚያበረታታው እንዴት ነው? አንተስ እንዲህ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
የይሖዋን በረከት ለማግኘት መታገላችሁን ቀጥሉ
የአምላክ ሕዝቦች የእሱን ሞገስ ለማግኘት ሲጥሩ በርካታ መሰናክሎች ቢያጋጥሟቸውም እነዚህን መሰናክሎች ይወጧቸዋል!
የአንባቢያን ጥያቄዎች
በዕብራውያን 4:12 ላይ “ሕያውና ኃይለኛ ነው” የተባለው “የአምላክ ቃል” ምንድን ነው?
በከፍተኛ ባለሥልጣናት ፊት ለምሥራቹ መሟገት
ሐዋርያው ጳውሎስ በወቅቱ ከነበረው የሕግ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ከወሰደው እርምጃ ትምህርት ማግኘት እንችላለን።
አለባበሳችሁ አምላክን ያስከብራል?
የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመሪያ ይሆኑናል።
በዛሬው ጊዜ ከይሖዋ መመሪያ ተጠቃሚ መሆን
በፖላንድ እና በፊጂ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ጥበብ የተንጸባረቀበት ውሳኔ አድርገዋል።
እናንት ወጣቶች፣ እምነታችሁን አጠናክሩ
የብዙኃኑን አመለካከት እንድትቀበል፣ ለምሳሌ በፈጣሪ ሳይሆን በዝግመተ ለውጥ እንድታምን ጫና እየተደረገብህ እንዳለ ይሰማሃል? ከሆነ በዚህ ርዕስ ላይ ጠቃሚ ሐሳብ ታገኛለህ።
እናንት ወላጆች፣ ልጆቻችሁ እምነት እንዲያዳብሩ እርዷቸው
አንዳንድ ጊዜ ይህ ኃላፊነት ከአቅማችሁ በላይ እንደሆነ ይሰማችኋል? በዚህ ረገድ ውጤታማ እንድትሆኑ የሚረዷችሁ አራት ነጥቦች በዚህ ርዕስ ላይ ቀርበዋል።