የጥናት ርዕስ 9
ወጣት ወንዶች—ሌሎች እምነት እንዲጥሉባችሁ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?
“[እንደ] ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት ከጎንህ ይሰለፋል።”—መዝ. 110:3
መዝሙር 39 በአምላክ ዘንድ ጥሩ ስም ማትረፍ
ማስተዋወቂያ *
1. ወጣት ወንድሞችን በተመለከተ ምን ማለት እንችላለን?
ወጣት ወንድሞች፣ በጉባኤ ውስጥ ልታከናውኑ የምትችሉት ብዙ ነገር አለ። ብዙዎቻችሁ ጥንካሬና ጉልበት አላችሁ። (ምሳሌ 20:29) ለጉባኤያችሁ ውድ ሀብት ናችሁ። ምናልባትም የጉባኤ አገልጋይ ሆናችሁ ለመሾም ትጓጉ ይሆናል። ሆኖም ሌሎች እንደ ልጅ አድርገው እንደሚመለከቷችሁ ሊሰማችሁ ይችላል፤ ወይም ደግሞ ‘ኃላፊነት ለመቀበል እንዳልደረስኩ አድርገው ይመለከቱኛል’ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ይሁንና ገና ልጅ ብትሆኑም እንኳ በጉባኤያችሁ ውስጥ ያሉትን ወንድሞችና እህቶች አመኔታና አክብሮት ለማትረፍ በአሁኑ ወቅት ልታደርጉ የምትችሏቸው ነገሮች አሉ።
2. በዚህ ርዕስ ውስጥ ምን እንመረምራለን?
2 በዚህ ርዕስ ውስጥ የንጉሥ ዳዊትን ሕይወት እንመረምራለን። በተጨማሪም የይሁዳ ነገሥታት የሆኑት አሳ እና ኢዮሳፍጥ ያጋጠሟቸውን ነገሮች በአጭሩ እንመለከታለን። እነዚህ ሦስት ሰዎች ያጋጠሟቸውን ፈተናዎችና የወሰዱትን እርምጃ እንመረምራለን፤ እንዲሁም ወጣት ወንድሞች ከእነሱ ምሳሌ ምን እንደሚማሩ እንመለከታለን።
ከንጉሥ ዳዊት ተማሩ
3. ወጣቶች በጉባኤ ውስጥ ያሉ አረጋውያንን መርዳት የሚችሉበት አንዱ መንገድ የትኛው ነው?
3 ዳዊት ወጣት ሳለ ሌሎችን የሚጠቅሙ ክህሎቶችን አዳብሮ ነበር። ዳዊት መንፈሳዊ ሰው እንደነበረ ጥያቄ የለውም፤ እንዲሁም የሙዚቃ ችሎታ ያዳበረ ሲሆን ይህን ተሰጥኦውን፣ በአምላክ የተሾመ ንጉሥ የሆነውን ሳኦልን በሚጠቅም 1 ሳሙ. 16:16, 23) ወጣቶች እናንተስ በጉባኤ ውስጥ ያሉ ወንድሞችንና እህቶችን የሚጠቅም ክህሎት አላችሁ? ብዙዎቻችሁ እንዲህ ያለ ችሎታ አላችሁ። ለምሳሌ አንዳንድ አረጋውያን ለግል ጥናት ወይም ለጉባኤ ስብሰባዎች ታብሌታቸውን ወይም የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻቸውን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የሚያሳያቸው ቢያገኙ ደስ ይላቸዋል። ከእነዚህ መሣሪያዎች ጋር በተያያዘ ያላችሁ እውቀት አረጋውያን ወንድሞቻችንን በጣም ይጠቅማቸዋል።
መልኩ ተጠቅሞበታል። (4. ወጣት ወንድሞች የዳዊትን ምሳሌ በመከተል የትኞቹን ባሕርያት ማዳበር ይኖርባቸዋል? (ሽፋኑን ተመልከት።)
4 ዳዊት በዕለት ተዕለት ሕይወቱ ኃላፊነት የሚሰማውና እምነት የሚጣልበት ሰው መሆኑን አሳይቷል። ለምሳሌ ወጣት ሳለ የአባቱን በጎች በትጋት ይንከባከብ ነበር። ይህ አደገኛ ሥራ ነበር። ከጊዜ በኋላ ዳዊት ንጉሥ ሳኦልን እንዲህ ብሎት ነበር፦ “አገልጋይህ የአባቱን መንጋ በሚጠብቅበት ጊዜ አንበሳ እንዲሁም ድብ ይመጣና ከመንጋው መካከል አንድ በግ ነጥቆ ይወስድ ነበር። እኔም ተከትዬው በመሄድ እመታውና በጉን ከአፉ አስጥለው ነበር።” (1 ሳሙ. 17:34, 35) ዳዊት ከበጎቹ ደህንነት ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ይሰማው ነበር፤ እንዲሁም እነሱን ከአደጋ ለማስጣል በድፍረት እርምጃ ወስዷል። ወጣት ወንድሞች የተሰጣቸውን ማንኛውንም ኃላፊነት በትጋት በመወጣት የዳዊትን ምሳሌ መከተል ይችላሉ።
5. በመዝሙር 25:14 መሠረት ወጣት ወንድሞች ሊያደርጉ የሚገባው ዋነኛው ነገር ምንድን ነው?
5 ወጣቱ ዳዊት ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መሥርቶ ነበር። ከዳዊት ድፍረት ወይም በገና ከመጫወት ችሎታው የበለጠ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ከይሖዋ ጋር ያለው ዝምድና ነው። ይሖዋ ለዳዊት አምላኩ ብቻ ሳይሆን የቅርብ ወዳጁም ነበር። (መዝሙር 25:14ን አንብብ።) ወጣት ወንድሞች፣ ልታደርጉ የሚገባው ዋነኛው ነገር በሰማይ ከሚኖረው አባታችሁ ጋር ያላችሁን ዝምድና ማጠናከር ነው። ይህ ደግሞ ተጨማሪ መብቶች እንድታገኙ ሊረዳችሁ ይችላል።
6. አንዳንዶች ስለ ዳዊት ምን አሉታዊ አመለካከት ነበራቸው?
6 ዳዊት ሌሎች ስለ እሱ ያላቸውን አሉታዊ አመለካከት ማሸነፍ ነበረበት። ለምሳሌ ዳዊት ጎልያድን ለመዋጋት ራሱን ባቀረበበት ጊዜ ንጉሥ ሳኦል “አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ” በማለት ሊያስቆመው ሞክሮ ነበር። (1 ሳሙ. 17:31-33) ከዚያ በፊት ደግሞ የገዛ ወንድሙ፣ ዳዊት ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት እንደፈጸመ በመናገር ተቆጥቶት ነበር። (1 ሳሙ. 17:26-30) ሆኖም ይሖዋ ዳዊትን ብስለት የጎደለው ወይም ኃላፊነት የማይሰማው እንደሆነ አድርጎ አልተመለከተውም። ይሖዋ ዳዊትን በሚገባ ያውቀው ነበር። ዳዊትም ወዳጁ ይሖዋ ብርታት እንደሚሰጠው በመተማመኑ ጎልያድን አሸንፎታል።—1 ሳሙ. 17:45, 48-51
7. ዳዊት ካጋጠመው ነገር ምን ትምህርት ታገኛላችሁ?
7 ዳዊት ካጋጠመው ነገር ምን ትምህርት ታገኛላችሁ? የዳዊት ታሪክ ትዕግሥት አስፈላጊ መሆኑን ያስተምራል። ከልጅነታችሁ ጀምሮ የሚያውቋችሁ ሰዎች እናንተን እንደ አዋቂ ለመመልከት ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል። ይሖዋ ግን ከውጫዊ ገጽታችሁ አልፎ እንደሚመለከት መተማመን ትችላላችሁ። ምን ዓይነት ሰው እንደሆናችሁና ምን የማድረግ ብቃት እንዳላችሁ ያውቃል። (1 ሳሙ. 16:7) በተጨማሪም ከአምላክ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት አጠናክሩ። ዳዊት እንዲህ ያደረገው የይሖዋን የፍጥረት ሥራዎች በትኩረት በመመልከት ነው። የፍጥረት ሥራዎች ስለ ይሖዋ ምን እንደሚያስተምሩት ቆም ብሎ ያሰላስል ነበር። (መዝ. 8:3, 4፤ 139:14፤ ሮም 1:20) ማድረግ የምትችሉት ሌላው ነገር ደግሞ ይሖዋ ብርታት እንዲሰጣችሁ መጠየቅ ነው። ለምሳሌ አብረዋችሁ የሚማሩ ልጆች የይሖዋ ምሥክር በመሆናችሁ ያሾፉባችኋል? እንዲህ ያለ ሁኔታ የሚያጋጥማችሁ ከሆነ ይሖዋ ይህንን ተፈታታኝ ሁኔታ ለመወጣት እንዲረዳችሁ ጸልዩ። እንዲሁም በአምላክ ቃል፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችን እና በቪዲዮዎቻችን ውስጥ የሚገኘውን ምክር በሥራ ላይ አውሉ። ይሖዋ አንድን ተፈታታኝ ሁኔታ እንድትወጡ የረዳችሁ እንዴት እንደሆነ በተመለከታችሁ ቁጥር በእሱ ይበልጥ እየተማመናችሁ ትሄዳላችሁ። ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በይሖዋ እንደምትተማመኑ ሲመለከቱ እምነት ይጥሉባችኋል።
8-9. ዳዊት ንጉሥ እስኪሆን ድረስ በትዕግሥት ለመጠበቅ የረዳው ምንድን ነው? ወጣት ወንድሞችስ ከእሱ ምሳሌ ምን ይማራሉ?
8 ዳዊት ያጋጠመውን ሌላ ተፈታታኝ ሁኔታም እንመልከት። ዳዊት ንጉሥ ለመሆን ከተቀባ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ እስኪሾም ድረስ ለበርካታ ዓመታት መጠበቅ ነበረበት። (1 ሳሙ. 16:13፤ 2 ሳሙ. 2:3, 4) በዚህ ጊዜ በትዕግሥት ለመጠበቅ የረዳው ምንድን ነው? ዳዊት ተስፋ ቆርጦ እጁን አጣጥፎ ከመቀመጥ ይልቅ ማድረግ በሚችለው ነገር ላይ አተኩሯል። ለምሳሌ በፍልስጤም ምድር በስደት ይኖር የነበረበትን ጊዜ የእስራኤልን ጠላቶች ለመዋጋት ተጠቅሞበታል። እንዲህ በማድረግ የይሁዳን ድንበር አስጠብቋል።—1 ሳሙ. 27:1-12
9 ወጣት ወንድሞች ከዳዊት ምሳሌ ምን ትምህርት ያገኛሉ? በአሁኑ ወቅት ያላችሁን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ወንድሞቻችሁን አገልግሉ። ሪካርዶ የተባለ ወንድም ያጋጠመውን ነገር እንደ ምሳሌ እንመልከት። * ሪካርዶ በአሥራዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ የዘወትር አቅኚ መሆን ይፈልግ ነበር። ሆኖም ሽማግሌዎች ለዚህ መብት እንደደረሰ አልተሰማቸውም። ሪካርዶ በዚህ ከመማረር ወይም ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በአገልግሎት የሚያደርገውን ተሳትፎ አሳደገ። እንዲህ ብሏል፦ “አሁን መለስ ብዬ ሳስበው ማሻሻያ ለማድረግ አጋጣሚ ማግኘቴ ጥሩ እንደነበረ ይሰማኛል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በሙሉ ተመልሼ ለመጠየቅና ለተመላልሶ መጠየቅ በደንብ ለመዘጋጀት ጥረት አደርግ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትም መምራት ችያለሁ። ተሞክሮ እያገኘሁ ስሄድ በራስ የመተማመን ስሜቴ አደገ።” ሪካርዶ በአሁኑ ጊዜ ውጤታማ የዘወትር አቅኚ እና የጉባኤ አገልጋይ ነው።
10. ዳዊት በአንድ ወቅት ትልቅ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት ምን አደረገ?
10 ዳዊት ያጋጠመውን ሌላ ሁኔታም እንመልከት። እሱና ሰዎቹ በስደት ይኖሩ በነበረበት ወቅት ቤተሰቦቻቸውን ትተው ለውጊያ ዘምተው ነበር። ወንዶቹ በሌሉበት በዚህ ወቅት የጠላት ሠራዊት ጥቃት በመሰንዘር ቤተሰቦቻቸውን በምርኮ ወሰደ። ዳዊት ልምድ ያለው ተዋጊ እንደመሆኑ መጠን በምርኮ የተያዙትን ለማስመለስ ውጤታማ የሆነ ስልት መቀየስ እንደማይከብደው ሊያስብ ይችል ነበር። ዳዊት ግን የይሖዋን እርዳታ ጠይቋል። አብያታር በተባለው ካህን አማካኝነት ዳዊት ይሖዋን 1 ሳሙ. 30:7-10) ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት ታገኛላችሁ?
“ይህን ወራሪ ቡድን ላሳደው?” ብሎ ጠየቀ። ይሖዋም ዳዊት ወራሪውን ቡድን እንዲያሳድድ የነገረው ሲሆን ውጤታማ እንደሚሆንም አረጋገጠለት። (11. ውሳኔ ከማድረጋችሁ በፊት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
11 ውሳኔ ከማድረጋችሁ በፊት የሌሎችን ምክር ጠይቁ። ወላጆቻችሁን አማክሩ። ተሞክሮ ካላቸው የጉባኤ ሽማግሌዎችም ጥሩ ምክር ማግኘት ትችላላችሁ። ይሖዋ እነዚህን የተሾሙ ወንዶች ይተማመንባቸዋል፤ እናንተም ልትተማመኑባቸው ትችላላችሁ። ይሖዋ የሚመለከታቸው ለጉባኤው እንደተሰጡ ‘ስጦታዎች’ አድርጎ ነው። (ኤፌ. 4:8) እነሱን በእምነታቸው መምሰላችሁና የሚሰጧችሁን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር ማዳመጣችሁ ይጠቅማችኋል። ከዚህ በመቀጠል ከንጉሥ አሳ ምን ትምህርት እንደምናገኝ እንመለከታለን።
ከንጉሥ አሳ ተማሩ
12. ንጉሥ አሳ መግዛት በጀመረበት ጊዜ የትኞቹ ባሕርያት ነበሩት?
12 ንጉሥ አሳ በወጣትነቱ ትሑትና ደፋር ነበር። ለምሳሌ በአባቱ በአቢያህ ምትክ ሲነግሥ የጣዖት አምልኮን ለማጥፋት እርምጃ ወስዶ ነበር። በተጨማሪም “የይሁዳ ሰዎች የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን እንዲፈልጉ እንዲሁም ሕጉንና ትእዛዙን እንዲያከብሩ” አዟል። (2 ዜና 14:1-7) ኢትዮጵያዊው ዛራ 1,000,000 ወታደሮችን አስከትሎ በይሁዳ ላይ በዘመተበት ጊዜ አሳ የይሖዋን እርዳታ በመጠየቅ የጥበብ እርምጃ ወስዷል። እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ሆይ፣ የምትረዳው ሕዝብ ብዛት ያለውም ይሁን ደካማ ለአንተ የሚያመጣው ለውጥ የለም። ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ እርዳን፤ በአንተ ታምነናልና።” ይህ ጸሎት አሳ፣ ይሖዋ እሱንም ሆነ ሕዝቡን የማዳን ችሎታ እንዳለው ምን ያህል እንደተማመነ የሚያሳይ ነው። አሳ በሰማይ በሚኖረው አባቱ ተማምኖ ነበር፤ ይሖዋም ‘ኢትዮጵያውያኑን ድል አደረጋቸው።’—2 ዜና 14:8-12
13. ከጊዜ በኋላ አሳ ምን ደረሰበት? ለምንስ?
13 አንድ ሚሊዮን ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት መጋፈጥ በጣም አስፈሪ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ሆኖም አሳ በይሖዋ በመታመኑ ድል አድርጓቸዋል። የሚያሳዝነው ግን አሳ ቀለል ያለ ፈተና ባጋጠመው ጊዜ ይሖዋን አላማከረም። ባኦስ የተባለው ክፉ የእስራኤል ንጉሥ በዘመተበት ወቅት አሳ የሶርያን ንጉሥ እርዳታ ጠየቀ። ይህ ውሳኔ አስከፊ ውጤት አስከትሏል! ይሖዋ በነቢዩ ሃናኒ አማካኝነት አሳን እንዲህ አለው፦ “በአምላክህ በይሖዋ ከመታመን ይልቅ በሶርያ ንጉሥ ስለታመንክ የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት ከእጅህ አምልጧል።” ደግሞም ከዚያ ጊዜ ወዲህ አሳ ጦርነት አልተለየውም። 2 ዜና 16:7, 9፤ 1 ነገ. 15:32) ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን?
(14. በይሖዋ እንደምትታመኑ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው? በ1 ጢሞቴዎስ 4:12 መሠረት በይሖዋ ከታመናችሁ ውጤቱ ምን ይሆናል?
14 ምንጊዜም ትሑት ሁኑ፤ እንዲሁም በይሖዋ መታመናችሁን ቀጥሉ። ስትጠመቁ ጠንካራ እምነት እንዳላችሁና በይሖዋ እንደምትተማመኑ አሳይታችኋል። ይሖዋም የቤተሰቡ አባል የመሆን መብት በመስጠት አክብሯችኋል። ከዚህ በኋላም በይሖዋ መታመናችሁን መቀጠል ይኖርባችኋል። በሕይወታችሁ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ ውሳኔዎችን ስታደርጉ በይሖዋ መታመን ቀላል ሊሆንላችሁ ይችላል። ይሁንና በሌሎች ጊዜያትስ? ከመዝናኛ ምርጫ፣ ከሰብዓዊ ሥራ እንዲሁም ከምታወጡት ግብ ጋር በተያያዘ ውሳኔዎች ስታደርጉ በይሖዋ መታመናችሁ ምንኛ አስፈላጊ ነው! በራሳችሁ ጥበብ አትመኩ። ከዚህ ይልቅ ከእናንተ ሁኔታ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ፈልጉ፤ ከዚያም በእነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች ተመሩ። (ምሳሌ 3:5, 6) እንዲህ ካደረጋችሁ የይሖዋን ልብ ታስደስታላችሁ እንዲሁም በጉባኤ ያሉ ወንድሞችና እህቶችን አክብሮት ታተርፋላችሁ።—1 ጢሞቴዎስ 4:12ን አንብብ።
ከንጉሥ ኢዮሳፍጥ ተማሩ
15. በ2 ዜና መዋዕል 18:1-3 እና 19:2 ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ምን ስህተቶች ሠርቷል?
15 እንደ ማንኛውም ሰው ሁሉ እናንተም ፍጹማን ስላልሆናችሁ አልፎ አልፎ ስህተት መሥራታችሁ አይቀርም። ሆኖም ይህ ሁኔታ በይሖዋ አገልግሎት አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ ከማድረግ ሊያግዳችሁ አይገባም። የንጉሥ ኢዮሳፍጥን ምሳሌ እንመልከት። ኢዮሳፍጥ በርካታ ግሩም ባሕርያት ነበሩት። ንጉሥ ሆኖ መግዛት በጀመረበት ወቅት “የአባቱን አምላክ ፈልጓል፤ ትእዛዙንም ተከትሏል።” በተጨማሪም በይሁዳ ከተሞች እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ስለ ይሖዋ እንዲያስተምሩ መኳንንቱን ልኳል። (2 ዜና 17:4, 7) ይሁን እንጂ ኢዮሳፍጥ ይሖዋን የማስደሰት ልባዊ ፍላጎት ቢኖረውም የተሳሳቱ ውሳኔዎች ያደረገባቸው ጊዜያት ነበሩ። በአንድ ወቅት ኢዮሳፍጥ የተሳሳተ ውሳኔ በማድረጉ ምክንያት አንድ የይሖዋ ወኪል ምክር ሰጥቶታል። (2 ዜና መዋዕል 18:1-3ን እና 19:2ን አንብብ።) ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት ታገኛላችሁ?
16. ከራጂቭ ተሞክሮ ምን ትምህርት ታገኛላችሁ?
16 ምክር ሲሰጣችሁ ተቀብላችሁ በሥራ ላይ አውሉት። እንደ ብዙዎቹ ወጣት ወንዶች እናንተም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት ከባድ ሊሆንባችሁ ይችላል። በዚህ ተስፋ አትቁረጡ። ራጂቭ በ1 ጢሞቴዎስ 4:8 ላይ በሚገኘው መሠረታዊ ሥርዓት ላይ ቆም ብዬ እንዳስብ ረዳኝ” ብሏል። ራጂቭ የተሰጠውን ምክር በትሕትና ተቀበለ፤ እንዲሁም በሕይወቱ ውስጥ ለየትኞቹ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት ቆም ብሎ አሰበ። “በሕይወቴ ውስጥ ለመንፈሳዊ ግቦች ቅድሚያ ለመስጠት ወሰንኩ” ብሏል። ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? “ይሄን ምክር ከተቀበልኩ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የጉባኤ አገልጋይ ሆኜ ተሾምኩ” በማለት ራጂቭ ተናግሯል።
የተባለን ወጣት ወንድም ተሞክሮ እንመልከት። ራጂቭ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለ ስለነበረው ሁኔታ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “አንዳንድ ጊዜ፣ በሕይወቴ ምን ማድረግ እንደምፈልግ ግራ ይገባኝ ነበር። እንደ ብዙዎቹ ወጣቶች ሁሉ ስብሰባ ከመሄድ ወይም አገልግሎት ከመውጣት ይበልጥ የሚያስደስተኝ ስፖርትና መዝናኛ ነበር።” ታዲያ ራጂቭን የረዳው ምንድን ነው? አንድ ሽማግሌ በአሳቢነት ተነሳስቶ ምክር ሰጠው። ራጂቭ “የሰማዩ አባታችሁ የሚኮራባችሁ ሰዎች ሁኑ
17. በዕድሜ ከፍ ያሉ ክርስቲያኖች ይሖዋን ስለሚያገለግሉ ወጣት ወንዶች ምን ይሰማቸዋል?
17 እናንት ወጣት ወንድሞች፣ በዕድሜ የሚበልጧችሁ ክርስቲያኖች ከእነሱ ጋር ‘እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ’ ይሖዋን በማገልገላችሁ ከልብ ያደንቋችኋል። (ሶፎ. 3:9) ቅንዓታችሁን እንዲሁም የተሰጣችሁን ሥራ ለማከናወን ያላችሁን ተነሳሽነት በጣም ያደንቃሉ። በእነሱ ዘንድ ሞገስ አግኝታችኋል።—1 ዮሐ. 2:14
18. በምሳሌ 27:11 መሠረት ይሖዋ እሱን ስለሚያገለግሉ ወጣት ወንዶች ምን ይሰማዋል?
18 ወጣት ወንድሞች፣ ይሖዋ እንደሚወዳችሁና እንደሚተማመንባችሁ ፈጽሞ አትዘንጉ። ይሖዋ በመጨረሻዎቹ ቀናት በገዛ ፈቃዱ ራሱን የሚያቀርብ የወጣት ወንዶች ሠራዊት እንደሚኖር ትንቢት አስነግሯል። (መዝ. 110:1-3) ይሖዋ እንደምትወዱትና አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ልታገለግሉት እንደምትፈልጉ ያውቃል። ስለዚህ ከራሳችሁም ሆነ ከሌሎች ጋር በተያያዘ ታጋሾች ሁኑ። ስህተት ስትሠሩ የሚሰጣችሁን ምክር እና ተግሣጽ ከይሖዋ እንደመጣ አድርጋችሁ ተቀበሉት። (ዕብ. 12:6) የሚሰጣችሁን ማንኛውንም ኃላፊነት በትጋት ተወጡ። ከሁሉ በላይ ደግሞ በምታደርጉት ነገር ሁሉ የሰማዩ አባታችሁ የሚኮራባችሁ ሰዎች ለመሆን ጥረት አድርጉ።—ምሳሌ 27:11ን አንብብ።
መዝሙር 135 የይሖዋ ፍቅራዊ ግብዣ፦ ‘ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን’