መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ግንቦት 2020

ይህ እትም ከሐምሌ 6–ነሐሴ 2, 2020 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመን

የጥናት ርዕስ 19፦ ከሐምሌ 6-12, 2020። ዳንኤል ‘የደቡቡን ንጉሥ’ እና ‘የሰሜኑን ንጉሥ’ አስመልክቶ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እያገኘ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስረጃዎችን እያየን ነው። ትንቢቱ እየተፈጸመ መሆኑን እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርገን ምንድን ነው? እንዲሁም የዚህን ትንቢት ዝርዝር ጉዳዮች መረዳት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

በፍጻሜው ዘመን የተነሱ ተቀናቃኝ ነገሥታት

ስለ ‘ሰሜኑ ንጉሥ’ እና ስለ “ደቡቡ ንጉሥ” የሚገልጸው ትንቢት ከሌሎች ትንቢቶች ጋር በተመሳሳይ ወቅት ፍጻሜውን የሚያገኝበት ጊዜ አለ። እነዚህ ትንቢቶች፣ ይህ ሥርዓት የሚጠፋበት ጊዜ እንደቀረበ የሚያረጋግጡት እንዴት ነው?

በዛሬው ጊዜ ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ ማን ነው?

የጥናት ርዕስ 20፦ ከሐምሌ 13-19, 2020። በዛሬው ጊዜ ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ ማን ነው? ወደ ፍጻሜው የሚመጣውስ እንዴት ነው? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ማወቃችን እምነታችንን ያጠናክርልናል፤ እንዲሁም በቅርቡ ለሚያጋጥሙን ፈተናዎች እንድንዘጋጅ ይረዳናል።

ከአምላክ ላገኘሃቸው ስጦታዎች አድናቆት አለህ?

የጥናት ርዕስ 21፦ ከሐምሌ 20-26, 2020። ይህ ርዕስ ለይሖዋ እና ከእሱ ላገኘናቸው አንዳንድ ስጦታዎች ያለን አድናቆት እንዲጨምር ያደርጋል። ከዚህም ሌላ አምላክ መኖሩን ለሚጠራጠሩ ሰዎች አሳማኝ ማስረጃ ለማቅረብ ይረዳናል።

በዓይን ለማይታዩት ውድ ሀብቶች አድናቆት አሳይ

የጥናት ርዕስ 22፦ ከሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 2, 2020። ቀደም ባለው ርዕስ ላይ፣ ከአምላክ ስላገኘናቸው በዓይን የሚታዩ አንዳንድ ውድ ሀብቶች ተመልክተናል። በዚህ ርዕስ ላይ ደግሞ በዓይን ስለማይታዩ ውድ ሀብቶች እንመለከታለን፤ ለእነዚህ ውድ ሀብቶች አድናቆታችንን እንዴት ማሳየት እንደምንችልም እናያለን። በተጨማሪም ይህ ርዕስ እንዲህ ያሉት ውድ ሀብቶች ምንጭ ለሆነው ለይሖዋ አምላክ ያለንን አድናቆት ለማሳደግም ይረዳናል።