መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥቅምት 2016

ይህ እትም ከኅዳር 28 እስከ ታኅሣሥ 25, 2016 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

የሕይወት ታሪክ

መልካም ምሳሌዎችን ለመከተል መጣጣር

የጎለመሱ ክርስቲያኖች የሚሰጡት ማበረታቻ፣ ሌሎች ክርስቲያኖች ጠቃሚ ግቦች እንዲያወጡና ግባቸው ላይ እንዲደርሱ ሊረዳቸው ይችላል። ቶማስ ማክሌን ሌሎች መልካም ምሳሌ የተዉለትና እሱም በበኩሉ ሌሎችን ለመርዳት ጥረት ያደረገው እንዴት እንደሆነ ይተርካል።

“ለእንግዶች ደግነት ማሳየትን አትርሱ”

አምላክ ለእንግዶች ምን አመለካከት አለው? የሌላ አገር ሰዎች ወደ ጉባኤያችሁ ሲመጡ እንግድነት እንዳይሰማቸው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

በሌላ አገር ስታገለግሉ መንፈሳዊነታችሁን ጠብቁ

ሁሉም ክርስቲያኖች የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን መንፈሳዊነት መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው። ያም ቢሆን በሌላ ቋንቋ በሚመራ ጉባኤ ውስጥ እያገለገላችሁ ከሆነ ለየት ያሉ ፈተናዎች ያጋጥሟችኋል።

‘ጥበብን ትጠብቃለህ?’

ጥበብ ከእውቀትና ከማስተዋል የሚለየው እንዴት ነው? ይህን ልዩነት ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።

በተስፋችሁ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ

በጥንት ዘመን የነበሩም ሆነ በዘመናችን የኖሩ ግሩም የእምነት ምሳሌዎች ጠንካራ እምነት እንድናዳብር ያበረታቱናል። አንተስ እምነትህ ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ በገባው ቃል ላይ እምነት እንዳላችሁ በተግባር አሳዩ

እምነት ምንድን ነው? እምነት እንዳለህ በተግባር ማሳየት የምትችለውስ እንዴት ነው?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

የሮም መንግሥት በመጀመሪያው መቶ ዘመን በይሁዳ ለነበሩ የአይሁድ ባለሥልጣናት ምን ያህል ሥልጣን ሰጥቶ ነበር? እንዲሁም በጥንት ዘመን አንድ ሰው በሌላ ሰው እርሻ ላይ እንክርዳድ መዝራቱ በእርግጥ ሊፈጸም የሚችል ነገር ነበር?