በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ቅድሚያ የሚሰጠውን ወስን

ማናችንም ብንሆን ለግል ጥናት ልናውል የምንችለው ጊዜ ውስን ነው። ታዲያ ይህን ጊዜ ጥሩ አድርገን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ፣ ጥድፊያ ውስጥ አትግባ። አለፍ አለፍ እያልክ ብዙ ነገር ከማንበብ ይልቅ ትንሽ ነገር ጊዜ ወስደህ ብታጠና የበለጠ ትጠቀማለህ።

ከዚያም ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር ወስን። (ኤፌ. 5:15, 16) ጠቃሚ ምክረ ሐሳቦች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦

  • መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ አንብብ። (መዝ. 1:2) በሳምንቱ መካከል ለሚደረገው ስብሰባ የተመደበው ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም እንደ መነሻ ሊሆንልህ ይችላል።

  • ለመጠበቂያ ግንብ ጥናትና በሳምንቱ መካከል ለሚደረገው ስብሰባ ተዘጋጅ። ሐሳብ ለመስጠት በሚያስችል መጠን ዝግጅት አድርግ።—መዝ. 22:22

  • ጊዜ ከተረፈህ ደግሞ በየጊዜው የሚወጡ ሌሎች መንፈሳዊ ምግቦችን ለመከታተል ጥረት አድርግ፤ ለሕዝብ የሚሰራጩ መጽሔቶችን፣ ቪዲዮዎችንና jw.org ላይ የሚወጡ ነገሮችን ለዚህ እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል።

  • የጥናት ፕሮጀክት መርጠህ አጥና። ለምሳሌ ያህል፣ ስላጋጠመህ ፈተና፣ ስለተፈጠረብህ ጥያቄ ወይም የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርህ ስለምትፈልገው አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳይ ምርምር ማድረግ ትችላለህ። ሐሳብ ለማግኘት jw.org ላይ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መልመጃዎች” የሚለውን ዓምድ ተመልከት።