መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መስከረም 2017
ይህ እትም ከጥቅምት 23 እስከ ኅዳር 26, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
ራስን የመግዛት ባሕርይን አዳብሩ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ምሳሌዎች ይህን ባሕርይ ለማዳበርና ለማንጸባረቅ የሚረዱን እንዴት ነው? ክርስቲያኖች ይህን ባሕርይ ማዳበር ያለባቸውስ ለምንድን ነው?
እንደ ይሖዋ ሩኅሩኅ ሁኑ
በአንድ ወቅት አምላክ ራሱን ለሙሴ ሲገልጥ ስሙንና ባሕርያቱን ነግሮታል። መጀመሪያ ላይ ከጠቀሳቸው ባሕርያት መካከል አንዱ ርኅራኄ ነው። ለመሆኑ ርኅራኄ ምንድን ነው? ስለዚህ ባሕርይ ይበልጥ ማወቃችን አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?
የሕይወት ታሪክ
መንፈሳዊ ከሆኑ ሰዎች ጋር በመሥራቴ ተባርኬያለሁ
ይህ የሕይወት ታሪክ፣ ዴቪድ ሲንክሌር ታማኝ ከሆኑ ወንድሞችና እህቶች ጋር በብሩክሊን ቤቴል ለ61 ዓመታት በማገልገል ስላሳለፈው አስደሳች ሕይወትና ስላገኛቸው መብቶች ይናገራል።
“የአምላካችን ቃል . . . ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”
መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓመታት አልፈዋል፤ ደግሞም የቋንቋ ለውጦች፣ ፖለቲካዊ ለውጦችና እንዳይተረጎም የተደረገው ጥረት የመጽሐፉን ሕልውና አደጋ ላይ ሊጥሉት ይችሉ ነበር። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ አሁንም ድረስ በብዛት በመሰራጨት ረገድ የመጀመሪያውን ደረጃ እንደያዘ ነው።
“የአምላክ ቃል . . . ኃይለኛ ነው”
በርካታ ሰዎች የአምላክን ቃል በማጥናታቸው በሕይወታቸው ላይ አስገራሚ ለውጥ አድርገዋል። የአምላክ ቃል በሕይወታችን ላይ ለውጥ እንዲያመጣ ከፈለግን ምን ማድረግ ይኖርብናል?
“ደፋር . . . ሁን፤ ሥራህንም ጀምር”
ድፍረት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? ይህን ባሕርይ ልናዳብር የምንችለውስ እንዴት ነው?