መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መስከረም 2019

ይህ እትም ከጥቅምት 28 እስከ ታኅሣሥ 1, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ይሖዋ ትሑት አገልጋዮቹን ከፍ አድርጎ ይመለከታል

ልናዳብራቸው ከሚገቡን በጣም አስፈላጊ ባሕርያት መካከል አንዱ ትሕትና ነው። ሁኔታችን ሲለወጥ ትሕትና ማሳየት ተፈታታኝ የሚሆንብን ለምንድን ነው?

አርማጌዶን—በጉጉት የምንጠብቀው ክንውን!

ከአርማጌዶን በፊት የሚፈጸሙት ዋና ዋና ክንውኖች የትኞቹ ናቸው? መጨረሻው እየቀረበ ሲሄድ ታማኝነታችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

ለይሖዋ በፈቃደኝነት ተገዙ

ሽማግሌዎች፣ አባቶችና እናቶች አገረ ገዢው ነህምያ፣ ንጉሥ ዳዊትና የኢየሱስ እናት ማርያም ከተዉት ምሳሌ ለይሖዋ ስለ መገዛት መማር ይችላሉ።

“ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ”

ኢየሱስ ያቀረበውን ግብዣ መቀበል ምን ነገሮችን ያካትታል? በዚህ ርዕስ ውስጥ የተጠቀሱትን ሦስት ነገሮች ካደረግን በኢየሱስ ቀንበር ሥር እረፍት ማግኘታችንን መቀጠል እንችላለን።

‘እነሆ፣ እጅግ ብዙ ሕዝብ’

ዮሐንስ ባየው ትንቢታዊ ራእይ ላይ ይሖዋ ከታላቁ መከራ የሚተርፈውንና በምድር ላይ ለዘላለም የሚኖረውን “እጅግ ብዙ ሕዝብ” ማንነትና ብዛት እንዲሁም ይህ ቡድን የተለያዩ ሰዎችን ያቀፈ መሆኑን አሳውቆናል።