በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ለልጆች የተዘጋጁ ፕሮጀክቶች

ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ይሖዋ የማስተማር ከባድ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። (ኤፌ. 6:4) የይሖዋ ድርጅት ወላጆችን የሚረዱ የተለያዩ መሣሪያዎችን አዘጋጅቷል። እነዚህን መሣሪያዎች ተጠቅማችሁ ልጆቻችሁን ማሠልጠን የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ያሉትን አማራጮች ተመልከቱ። JW.ORG ቪዲዮዎችንና መልመጃዎችን ጨምሮ ለልጆች የተዘጋጁትን ነገሮች በሙሉ ይዟል። a እነዚህን ነገሮች ለማግኘት በመፈለጊያ ሣጥኑ ላይ “ልጆች” ወይም “ወጣቶች” ብላችሁ ጻፉ።

  • ለልጆቻችሁ የሚሆናቸውን ነገር ምረጡ። “ልጆች” ከሚለው ክፍል ውስጥ ለልጆቻችሁ የሚጠቅም ቪዲዮ፣ መዝሙር ወይም መልመጃ መምረጥ ትችላላችሁ። እነዚህን ነገሮች ለማግኘት በመፈለጊያ ሣጥኑ ላይ “የቤተሰብ አምልኮ ፕሮጀክት” ብላችሁ ጻፉ።

  • አወያዩአቸው። ቪዲዮዎቹንና መልመጃዎቹን የምትጠቀሙባቸው የልጆቻችሁን ጊዜና ትኩረት እንዲይዙላችሁ ብቻ ሊሆን አይገባም። ከዚህ ይልቅ፣ ከልጆቻችሁ ጋር ተወያዩባቸው፤ እንዲሁም ልጆቻችሁ ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት እንዲመሠርቱ እርዷቸው።

a በአሁኑ ወቅት JW Library® ላይ ለልጆች የተዘጋጁት ቪዲዮዎች በሙሉ የሚገኙ ቢሆንም ከመልመጃዎቹ መካከል እዚያ የሚገኙት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው።