በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

አእምሮህን ክፍት አድርገህ አጥና

አእምሮህን ክፍት አድርገህ አጥና

ለማጥናት ስንዘጋጅ ከጥናቱ አገኛለሁ ብለን የምንጠብቀው ትምህርት ይኖራል። ይሁንና ይሖዋ ከጠበቅነው የተለየ ነገር ሊያስተምረን እንደሚችል መዘንጋት የለብንም። ታዲያ አእምሯችንን ክፍት አድርገን ማጥናት የምንችለው እንዴት ነው?

ጥበብ ለማግኘት ጸልይ። ይሖዋ ዛሬ ሊያስተምርህ የፈለገውን ነገር ለማስተዋል እንዲረዳህ ጸልይ። (ያዕ. 1:5) ቀደም ሲል በምታውቀው ነገር ብቻ ረክተህ አትቀመጥ።—ምሳሌ 3:5, 6

መጽሐፍ ቅዱስ አስደናቂ ኃይል እንዳለው አስታውስ። “የአምላክ ቃል ሕያው . . . ነው።” (ዕብ. 4:12) “ሕያው” የሆነው የአምላክ ቃል ባነበብነው ቁጥር በተለያየ መንገድ ሊቀርጸን ይችላል፤ ከእኛ የሚጠበቀው በምናነብበት ወቅት ቃሉ ለሚያስተምረን ነገር አእምሯችንን ክፍት ማድረግ ነው።

በይሖዋ ማዕድ ላይ ለቀረበው ነገር በሙሉ አድናቆት ይኑርህ። እሱ የሚያቀርብልን መንፈሳዊ ምግብ ‘ምርጥ ምግቦች እንደሚገኙበት ታላቅ ግብዣ’ ነው። (ኢሳ. 25:6) አልወደውም በሚል አንዳንድ ‘ምግቦችን’ እንዳትተው ተጠንቀቅ። እንዲህ ካደረግክ፣ አምላክ ከሚያቀርበው ምግብ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ከልብህ መደሰትም ትችላለህ!