መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2018

ይህ እትም ከሚያዝያ 30 እስከ ሰኔ 3, 2018 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ጥምቀት—ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ ብቃት

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጥምቀት ምን ይላል? አንድ ሰው ከመጠመቁ በፊት የትኞቹን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርበታል? ልጃችንን አሊያም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን በምናስጠናበት ጊዜ፣ ጥምቀት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን በአእምሯችን መያዝ ያለብንስ ለምንድን ነው?

ወላጆች፣ ልጆቻችሁን እድገት አድርገው እንዲጠመቁ እየረዳችኋቸው ነው?

ክርስቲያን ወላጆች፣ ልጆቻቸው ከመጠመቃቸው በፊት ምን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የይሖዋ ምሥክሮች ሐዋርያው ጳውሎስን ራሰ በራ እንደሆነ አድርገው የሚሥሉት ለምንድን ነው?

እንግዳ ተቀባይነት—በጣም አስፈላጊ የሆነ ባሕርይ!

ቅዱሳን መጻሕፍት ክርስቲያኖች አንዳቸው ሌላውን በእንግድነት እንዲቀበሉ የሚያበረታቱት ለምንድን ነው? የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ማሳየት የምንችልባቸው አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እንዳናሳይ እንቅፋት የሚሆኑብንን ነገሮች እንዴት ማሸነፍ እንችላለን?

የሕይወት ታሪክ

ይሖዋ ፈጽሞ አልተወኝም!

ኤሪካ ኔረር ብራይት በዘወትር አቅኚነት፣ በልዩ አቅኚነትና በሚስዮናዊነት አገልግላለች። አምላክን በታማኝነት ባገለችባቸው በርካታ ዓመታት በሙሉ እሱ እንዴት እንደደገፋት፣ እንዳበረታትና አጥብቆ እንደያዛት ትተርካለች።

ተግሣጽ—የአምላክ ፍቅር መግለጫ

አምላክ በጥንት ዘመን ተግሣጽ ከሰጣቸው ሰዎች ምን ትምህርት እናገኛለን? ተግሣጽ መስጠት በሚያስፈልገን ጊዜ የይሖዋን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

“ተግሣጽን ስሙ፤ ጥበበኞችም ሁኑ”

ይሖዋ ራሳችንን እንድንገሥጽ የሚያስተምረን በየትኞቹ መንገዶች ነው? በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ከሚሰጠን ከየትኛውም ተግሣጽ ጥቅም ማግኘት የምንችለውስ እንዴት ነው?