በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

“ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚለውን ገጽታ በሚገባ መጠቀም

JW ላይብረሪ እና jw.org ላይ የሚገኘው “ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚለው ገጽታ በቅርቡ የወጡ ርዕሶችንና ቪዲዮዎችን ያሳያል። ይህን ገጽታ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ልትጠቀሙበት የምትችሉት እንዴት ነው?

JW ላይብረሪ

  • አዳዲስ ርዕሶች ሲወጡ ርዕሶቹን የያዘው ዓምድ “ምን አዲስ ነገር አለ?” በሚለው ክፍል ሥር እንደ አዲስ ይታያል። ዓምዱን በማውረድ በዚያ ዓምድ ሥር በቅርቡ የወጣውን ርዕስ ማግኘት ትችላላችሁ። ርዕሱ በጊዜ ቅደም ተከተል በተቀመጠው ዝርዝር ውስጥ ከላይ ይገኛል።

  • እንደ መጽሔት ያሉ ረዘም ያሉ ጽሑፎችን በአንድ ዙር አንብባችሁ አትጨርሱ ይሆናል። አንብባችሁ ያልጨረሳችሁትን መጽሔት በቀላሉ ማግኘት እንድትችሉ መጽሔቱን አንብባችሁ እስክትጨርሱ ድረስ “ፈጣን መዳረሻ” የሚለው ውስጥ ልታስገቡት ትችላላችሁ።

JW.ORG

ዜናዎችንና ማስታወቂያዎችን ጨምሮ አንዳንድ መረጃዎች የሚገኙት jw.org ድረ ገጽ ላይ ብቻ ነው፤ JW ላይብረሪ ላይ አይገኙም። አዳዲስ ርዕሶችን ለማግኘት ድረ ገጹ ላይ የሚገኘውን “ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚለውን ገጽ አዘውትራችሁ መጎብኘታችሁን አትርሱ።