መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሚያዝያ 2018
ይህ እትም ከሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 8, 2018 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
እውነተኛ ነፃነት የሚያስገኘው መንገድ
አንዳንዶች ከጭቆና፣ ከአድልዎና ከድህነት ነፃ መውጣት ይፈልጋሉ። ሌሎች ደግሞ የመናገርና የመምረጥ ነፃነት እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ። እውነተኛ ነፃነት ማግኘት ይቻላል?
የነፃነት አምላክ የሆነውን ይሖዋን አገልግሉ
የይሖዋ መንፈስ ነፃ ያወጣን እንዴት ነው? አምላክ የሰጠንን ነፃነት ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዳንጠቀምበት መጠንቀቅ የምንችለው እንዴት ነው?
የተሾማችሁ ወንዶች—ከጢሞቴዎስ ተማሩ
ጢሞቴዎስ ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር አብሮ ማገልገል በጀመረበት ወቅት በራስ የመተማመን ስሜት ይጎድለው የነበረ ይመስላል። የጉባኤ ሽማግሌዎችና አገልጋዮች ጢሞቴዎስ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ?
ማበረታቻ በመስጠት ረገድ ግሩም ምሳሌ የሆነውን ይሖዋን ምሰሉ
በጥንት ዘመን የኖሩ የይሖዋ ሕዝቦች ማበረታቻ እንዳስፈለጋቸው ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉትም ማበረታቻ ያስፈልጋቸዋል።
“ከበፊቱ ይበልጥ” እርስ በርስ እንበረታታ
የይሖዋ ቀን ከመቅረቡ አንጻር፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ወንድሞቻችንን ማበረታታት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት መስጠት ያስፈልገናል።
እናንት ወጣቶች፣ ትኩረታችሁ ያረፈው በመንፈሳዊ ግቦች ላይ ነው?
ወጣቶች በፊታቸው የተደቀኑት ውሳኔዎችና የሚቀርቡላቸው አጋጣሚዎች አንዳንድ ጊዜ ግራ ሊያጋቧቸው ይችላሉ። የወደፊት ሕይወታቸውን በተመለከተ ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው?
የአንባቢያን ጥያቄዎች
የይሖዋ ምሥክሮችን ጽሑፎች በግል ወይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ማውጣት የማይፈቀደው ለምንድን ነው?
የአንባቢያን ጥያቄዎች
መዝሙር 144 የሚናገረው ስለ እነማን ነው?