መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሰኔ 2017
ይህ እትም ከሐምሌ 31 እስከ ነሐሴ 27, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
ታስታውሳለህ?
በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት እትሞች አንብበሃቸዋል? ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ምን ያህሉን መመለስ እንደምትችል እስቲ ተመልከት።
ይሖዋ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል
በዛሬው ጊዜ ክርስቲያኖች ከትዳርና ከቤተሰብ ሕይወት ጋር በተያያዘ ምን ፈተናዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ? እንዲህ ያሉ ፈተናዎች አጋጥመውህ ከሆነ አምላክ ሊያጽናናህ የሚችለው እንዴት ነው?
ልባችሁ በመንፈሳዊ ሀብት ላይ ያተኮረ ይሁን
ከፍ አድርገን ልንመለከታቸው የሚገቡ መንፈሳዊ ሀብቶች የትኞቹ ናቸው? ይህንንስ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ከሰዎች ውጫዊ ገጽታ ባሻገር ለመመልከት ትሞክራላችሁ?
አንድ የይሖዋ ምሥክር ፈጽሞ ሰው እንዲቀርበው የማይፈልግን አስቸጋሪ የሆነ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በትዕግሥት ማናገሩ ምን ውጤት አስገኘ?
አለመግባባቶችን በመፍታት ሰላም ለመፍጠር ጥረት ታደርጋለህ?
ሰዎች ሰላም እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ይሁንና ብዙዎች ጥቃት እንደተሰነዘረባቸውና ክብራቸው እንደተነካ ሲሰማቸው ሰላም የሚያደፈርስ ነገር ማድረግ ይጀምራሉ። እንዲህ ከማድረግ እንድትቆጠብ ምን ሊረዳህ ይችላል?
’ማስተዋልሽ የተባረከ ይሁን!’
እነዚህ ቃላት በጥንቷ እስራኤል ይኖር የነበረው ዳዊት አቢጋኤልን ለማመስገን የተናገራቸው ናቸው። ዳዊት አቢጋኤልን ያመሰገናት ለምንድን ነው? እኛስ ከእሷ ምን እንማራለን?
ትኩረታችሁን አንገብጋቢ በሆነው ጉዳይ ላይ አድርጉ
በሰው ልጆች ሁሉ ፊት የተደቀነው አንገብጋቢ ጉዳይ ምንድን ነው? ይህን ጉዳይ ማወቅህ አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?
የይሖዋን ሉዓላዊነት ደግፉ!
ይሖዋ ጽንፈ ዓለሙን የመግዛት መብት እንዳለው አምነህ መቀበልህ በሕይወትህ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንስሳት ይሸጡ የነበሩትን ነጋዴዎች “ዘራፊዎች” ብሎ የጠራቸው ለምንድን ነው?