መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሰኔ 2019

ይህ እትም ከነሐሴ 5 እስከ መስከረም 1, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

“ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ”!

ሰይጣን ሰዎችን በማታለል ረገድ ተወዳዳሪ የለውም። አስተሳሰባችንን ለማዛባትና ለይሖዋ ጀርባችንን እንድንሰጥ ለማድረግ የሚሞክረው እንዴት ነው?

ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውቀት የሚጻረርን ማንኛውንም የተሳሳተ ሐሳብ አፍርሱ!

ያሳለፍነው ሕይወት፣ ባሕላችን እንዲሁም የቀሰምነው ትምህርት በአስተሳሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እንደ “ምሽግ” ጠንካራ የሆኑና ሥር የሰደዱ የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው?

የሚያስጨንቁ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟችሁ በይሖዋ ታመኑ

ከልክ ያለፈ ወይም ረዘም ላለ ጊዜ የሚዘልቅ ጭንቀት በአካላችንም ሆነ በስሜታችን ላይ ጉዳት ያስከትላል። ይሖዋ፣ በጥንት ዘመን የነበሩ አገልጋዮቹ አስጨናቂ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ መመርመራችን ይጠቅመናል።

የሚያስጨንቁ ሁኔታዎች ያጋጠሟቸውን እርዷቸው

ሎጥ፣ ኢዮብና ናኦሚ ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ቢሆኑም በሕይወታቸው ውስጥ አስጨናቂ ሁኔታዎች ያጋጠሟቸው ጊዜያት ነበሩ። እነሱ ካጋጠማቸው ነገር ምን እንማራለን?

ከሰይጣን ወጥመድ አስተማማኝ ጥበቃ ማግኘት

የብልግና ምስሎችን መመልከትና እንዲህ ዓይነት ጽሑፎችን ማንበብ ለበርካታ የአምላክ አገልጋዮች ወጥመድ ሆኖባቸዋል። እንዲህ ካለው ርኩስ ልማድ መራቅ የምትችለው እንዴት ነው?

አንድን ጥንታዊ ጥቅልል ማንበብ ተቻለ

በ1970 የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች፣ እስራኤል ውስጥ አንድ የተቃጠለ ጥቅልል ቆፍረው አወጡ። የተራቀቀ ምስል ማንሻ መሣሪያ (3-D ስካነር) በመጠቀም፣ በጥቅልሉ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ምስል ማንሳት ተቻለ። ታዲያ ምን ተገኘ?