በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጥናት ርዕስ 49

ለዘላለም መኖር እንችላለን

ለዘላለም መኖር እንችላለን

“[ይህ] የዘላለም ሕይወት ነው።”—ዮሐ. 17:3

መዝሙር 147 የዘላለም ሕይወት ተስፋ ተሰጥቶናል

ማስተዋወቂያ a

1. ይሖዋ በሰጠን የዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ ማሰላሰላችን ምን እንዲሰማን ያደርጋል?

 ይሖዋ እሱን የሚታዘዙ ሰዎች “የዘላለም ሕይወት” እንደሚያገኙ ቃል ገብቷል። (ሮም 6:23) ይሖዋ በሰጠን ተስፋ ላይ ስናሰላስል ለእሱ ያለን ፍቅር ያድጋል። እስቲ አስቡት፦ የሰማዩ አባታችን በጣም ስለሚወደን ፈጽሞ ከእሱ ሳንለይ መኖር የምንችልበት አጋጣሚ ከፍቶልናል።

2. የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚረዳን እንዴት ነው?

2 አምላክ የሰጠን የዘላለም ሕይወት ተስፋ በአሁኑ ጊዜ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጽናት እንድንቋቋም ይረዳናል። ጠላቶቻችን እንደሚገድሉን ቢዝቱብን እንኳ አቋማችንን አናላላም። ለምን? አንዱ ምክንያት፣ ለይሖዋ ታማኝ ሆነን ከሞትን እሱ ከሞት እንደሚያስነሳንና ዳግመኛ ያለመሞት ተስፋ እንደሚሰጠን ስለምናውቅ ነው። (ዮሐ. 5:28, 29፤ 1 ቆሮ. 15:55-58፤ ዕብ. 2:15) ይሁንና ለዘላለም መኖር እንደምንችል እርግጠኛ የምንሆነው ለምንድን ነው? አንዳንድ ምክንያቶችን እስቲ እንመልከት።

ይሖዋ ለዘላለም ይኖራል

3. ይሖዋ ለዘላለም ሊያኖረን እንደሚችል እርግጠኛ መሆን የምንችለው ለምንድን ነው? (መዝሙር 102:12, 24, 27)

3 ይሖዋ ለዘላለም ሊያኖረን እንደሚችል እናውቃለን፤ ምክንያቱም እሱ የሕይወት ምንጭ ከመሆኑም ሌላ ለዘላለም ይኖራል። (መዝ. 36:9) ይሖዋ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ እንደሌለው ከሚያሳዩ ጥቅሶች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ እስቲ እንመልከት። መዝሙር 90:2 ይሖዋ “ከዘላለም እስከ ዘላለም” እንደሚኖር ይናገራል። መዝሙር 102ም ተመሳሳይ ሐሳብ ይዟል። (መዝሙር 102:12, 24, 27ን አንብብ።) በተጨማሪም ነቢዩ ዕንባቆም ስለ ሰማዩ አባታችን እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከዘላለም አንስቶ ያለህ አይደለህም? ቅዱስ የሆንከው አምላኬ ሆይ፣ አንተ አትሞትም።”ዕን. 1:12

4. ይሖዋ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ እንደሌለው የሚገልጸውን ሐሳብ መረዳት አለመቻላችን ሊያሳስበን ይገባል? አብራራ።

4 ይሖዋ “ከዘላለም እስከ ዘላለም” እንደሚኖር የሚገልጸውን ሐሳብ መረዳት ይከብዳችኋል? (ኢሳ. 40:28) እንዲህ ቢሰማችሁ አያስገርምም። ኤሊሁ ስለ አምላክ ሲናገር “የዘመኑም ቁጥር ከመረዳት ችሎታ በላይ ነው” ብሏል። (ኢዮብ 36:26) ሆኖም አንድን ነገር መረዳት ስላልቻልን ብቻ ያ ነገር ውሸት ነው ማለት አይደለም። ለምሳሌ የብርሃን ምንነት ሙሉ በሙሉ አይገባን ይሆናል። ታዲያ ይህ ሲባል ብርሃን የሚባል ነገር የለም ማለት ነው? በጭራሽ! በተመሳሳይም እኛ የሰው ልጆች፣ ይሖዋ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ እንደሌለው የሚገልጸውን ሐሳብ መቼም ቢሆን ሙሉ በሙሉ መረዳት አንችል ይሆናል። ሆኖም ይህ ሲባል፣ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አይኖርም ማለት አይደለም። የፈጣሪያችን ማንነት በእኛ የመረዳት ችሎታ የተገደበ አይደለም። (ሮም 11:33-36) እሱ እንደ ፀሐይ ያሉ የብርሃን ምንጮችን ጨምሮ ግዑዙ ጽንፈ ዓለም ወደ ሕልውና ከመምጣቱ በፊት ነበር። ይሖዋ “ምድርን በኃይሉ የሠራው” እሱ እንደሆነ ገልጾልናል። አዎ፣ ‘ሰማያትን ከመዘርጋቱ’ በፊት እሱ ነበር። (ኤር. 51:15፤ ሥራ 17:24) ለዘላለም መኖር እንደምንችል እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርገን ሌላው ምክንያትስ ምንድን ነው?

የተፈጠርነው ለዘላለም እንድንኖር ነው

5. አዳምና ሔዋን ምን አጋጣሚ ነበራቸው?

5 ከሰዎች በስተቀር በምድር ላይ ያሉ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ የተፈጠሩት ለዘላለም እንዲኖሩ አይደለም። ለሰዎች ግን ይሖዋ ያለመሞት ልዩ መብት ሰጥቷቸው ነበር። ይሁንና አዳምን እንዲህ በማለት አስጠንቅቆታል፦ “ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ግን አትብላ፤ ምክንያቱም ከዚህ ዛፍ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።” (ዘፍ. 2:17) አዳምና ሔዋን ይሖዋን ቢታዘዙ ኖሮ አይሞቱም ነበር። ውሎ አድሮ ይሖዋ “ከሕይወት ዛፍ” እንዲበሉ ይፈቅድላቸው ነበር ብሎ መደምደም ምክንያታዊ ነው። ከሕይወት ዛፍ መብላታቸው ለዘላለም እንደሚኖሩ ይሖዋ ዋስትና እንደሰጣቸው ያመለክታል። bዘፍ. 3:22

6-7. (ሀ) ሰዎች የተፈጠሩት ለመሞት እንዳልሆነ የሚጠቁመው ሌላው ማስረጃ ምንድን ነው? (ለ) ወደፊት የትኞቹን ነገሮች ለማድረግ ትጓጓለህ? (ሥዕሎቹን ተመልከት።)

6 አንዳንድ ተመራማሪዎች፣ አንጎላችን በአሁኑ የሕይወት ዘመናችን ልንሰበስብ ከምንችለው እጅግ የሚበልጥ መረጃ የማከማቸት አቅም እንዳለው የሚገልጽ ሳይንሳዊ ማስረጃ ያቀርባሉ፤ ይህም ትኩረት የሚስብ ነው። በ2010 አንድ መጽሔት፣ አንጎላችን 2.5 ሚሊዮን ጊጋባይት ገደማ የሚሆን መረጃ የመያዝ አቅም እንዳለው ገልጾ ነበር፤ ይህም ሦስት ሚሊዮን ሰዓት (ከ300 ዓመት በላይ) ርዝመት ካለው ቪዲዮ ጋር እኩል ነው። ይሁንና አንጎላችን ከዚህ እጅግ የበለጠ መረጃም መያዝ ይችል ይሆናል። ይህ ግኝት፣ ይሖዋ አንጎላችንን የፈጠረው በ70 ወይም በ80 ዓመት ልንሰበስብ ከምንችለው እጅግ የበለጠ መረጃ መያዝ እንዲችል አድርጎ እንደሆነ ያሳያል።—መዝ. 90:10

7 ከዚህም ሌላ፣ ይሖዋ የፈጠረን በሕይወት የመቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት እንዲኖረን አድርጎ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው ልጆች ሲናገር “[አምላክ] ዘላለማዊነትን በልባቸው ውስጥ አኑሯል” ይላል። (መክ. 3:11) ሞትን እንደ ጠላት የምንመለከትበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። (1 ቆሮ. 15:26) በጠና ብንታመም ሁኔታውን ተቀብለን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን? በፍጹም። አብዛኞቻችን ሐኪም ጋ መሄዳችን፣ ምናልባትም ከበሽታው ለመዳን መድኃኒት መውሰዳችን አይቀርም። እንዲያውም ከሞት ለማምለጥ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። በተጨማሪም የምንወደው ሰው ሲሞት፣ ግለሰቡ ወጣትም ሆነ አረጋዊ ጥልቅ የሆነ የስሜት ሥቃይ ይሰማናል። (ዮሐ. 11:32, 33) በእርግጥም የሚወደን ፈጣሪያችን፣ ሰዎች ለዘላለም እንዲኖሩ ዓላማው ባይሆን ኖሮ ለዘላለም የመኖር ፍላጎትም ሆነ አቅም አይሰጠንም ነበር። ሆኖም የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንደምንችል የሚያረጋግጡ ሌሎች አሳማኝ ምክንያቶችም አሉን። ይሖዋ ጥንትም ሆነ ዛሬ ያደረጋቸውን አንዳንድ ነገሮች እስቲ እንመልከት፤ እነዚህ ነገሮች ይሖዋ ለሰው ልጆች ያለውን የመጀመሪያ ዓላማ እንዳልቀየረ ያሳያሉ።

የዘላለም ሕይወት ተስፋ ስለተዘረጋልን ወደፊት ማድረግ ስለምንችላቸው ነገሮች እያሰብን መደሰት እንችላለን (አንቀጽ 7⁠ን ተመልከት) c

የይሖዋ ዓላማ አልተቀየረም

8. ይሖዋ ለእኛ ያለውን ዓላማ በተመለከተ ኢሳይያስ 55:11 ምን ዋስትና ይሰጠናል?

8 አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራት በልጆቻቸው ላይ ሞት ቢያመጡም እንኳ ይሖዋ ለሰዎች ያለውን ዓላማ አልቀየረም። (ኢሳይያስ 55:11ን አንብብ።) አሁንም ቢሆን ዓላማው ታማኝ ሰዎች ለዘላለም እንዲኖሩ ነው። ይሖዋ ዓላማውን ለመፈጸም ሲል የተናገራቸውንና ያደረጋቸውን ነገሮች መመርመራችን እዚህ መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ያደርገናል።

9. አምላክ ምን ቃል ገብቷል? (ዳንኤል 12:2, 13)

9 ይሖዋ ሙታንን እንደሚያስነሳና ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል። (ሥራ 24:15፤ ቲቶ 1:1, 2) ታማኙ ኢዮብ፣ ይሖዋ የሞቱትን ለማስነሳት እንደሚናፍቅ እርግጠኛ ነበር። (ኢዮብ 14:14, 15) ነቢዩ ዳንኤል፣ ሰዎች ከሞት ተነስተው የዘላለም ሕይወት የማግኘት አጋጣሚ እንደሚኖራቸው ያውቅ ነበር። (መዝ. 37:29፤ ዳንኤል 12:2, 13ን አንብብ።) በኢየሱስ ዘመን የነበሩት አይሁዳውያንም፣ ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ “የዘላለም ሕይወት” እንደሚሰጣቸው ያውቁ ነበር። (ሉቃስ 10:25፤ 18:18) ኢየሱስ ስለዚህ ተስፋ በተደጋጋሚ ተናግሯል፤ እሱንም ቢሆን አባቱ ከሞት አስነስቶታል።—ማቴ. 19:29፤ 22:31, 32፤ ሉቃስ 18:30፤ ዮሐ. 11:25

ኤልያስ የፈጸመው ትንሣኤ ምን ዋስትና ይሰጥሃል? (አንቀጽ 10⁠ን ተመልከት)

10. በጥንት ዘመን የተከናወኑ ትንሣኤዎች ምን ያረጋግጣሉ? (ሥዕሉን ተመልከት።)

10 የሕይወት ምንጭ የሆነው ይሖዋ ሰዎችን ከሞት የማስነሳት ኃይል አለው። ነቢዩ ኤልያስ የሰራፕታዋን መበለት ልጅ ከሞት እንዲያስነሳ ኃይል ሰጥቶታል። (1 ነገ. 17:21-23) ከጊዜ በኋላም ነቢዩ ኤልሳዕ በአምላክ እርዳታ የሱናማዊቷን ልጅ ከሞት አስነስቶታል። (2 ነገ. 4:18-20, 34-37) እነዚህና ሌሎች ትንሣኤዎች፣ ይሖዋ ሰዎችን ከሞት የማስነሳት ኃይል እንዳለው ያረጋግጣሉ። ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት አባቱ እንዲህ ያለ ኃይል እንደሰጠው አሳይቷል። (ዮሐ. 11:23-25, 43, 44) አሁን ኢየሱስ በሰማይ ላይ ሲሆን “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር” ተሰጥቶታል። በመሆኑም “በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ” እንደሚነሱና ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ እንደሚያገኙ የገባውን ቃል ለመፈጸም የሚያስችል ሥልጣን አለው።—ማቴ. 28:18፤ ዮሐ. 5:25-29

11. ቤዛው ለዘላለም መኖር የምንችልበትን በር የከፈተልን እንዴት ነው?

11 ይሖዋ የሚወደው ልጁ ተሠቃይቶ እንዲሞት የፈቀደው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ምክንያቱን ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።” (ዮሐ. 3:16) አምላክ ልጁን ኃጢአታችንን የሚሸፍን ቤዛ አድርጎ በመስጠት የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምንችልበት በር ከፍቶልናል። (ማቴ. 20:28) ሐዋርያው ጳውሎስ የአምላክ ዓላማ ወሳኝ ክፍል ስለሆነው ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ሞት የመጣው በአንድ ሰው በኩል ስለሆነ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል ነው። ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉና።”—1 ቆሮ. 15:21, 22

12. ይሖዋ ለእኛ ያለውን ዓላማ የሚፈጽመው እንዴት ነው?

12 ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ የአምላክ መንግሥት እንዲመጣና የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል። (ማቴ. 6:9, 10) የአምላክ ዓላማ አንዱ ክፍል፣ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ ነው። ይሖዋ ይህን ዓላማውን ለማስፈጸም ልጁን የመሲሐዊው መንግሥት ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። አምላክ ፈቃዱን ለማስፈጸም ከኢየሱስ ጋር የሚሠሩ 144,000 ሰዎችን ከምድር ሲሰበስብ ቆይቷል።—ራእይ 5:9, 10

13. ይሖዋ በአሁኑ ወቅት ምን እያደረገ ነው? እናንተስ የበኩላችሁን ድርሻ እየተወጣችሁ ያላችሁት እንዴት ነው?

13 በአሁኑ ወቅት ይሖዋ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” በመሰብሰብ የመንግሥቱ ተገዢዎች እንዲሆኑ እያሠለጠናቸው ነው። (ራእይ 7:9, 10፤ ያዕ. 2:8) በዛሬው ጊዜ ያለው ዓለም በጥላቻና በጦርነት የተከፋፈለ ቢሆንም እንኳ የዚህ ቡድን አባላት ማንኛውንም የብሔር፣ የዘርና የግል ጥላቻ ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። አሁንም ቢሆን በምሳሌያዊ ሁኔታ ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ እያደረጉ ነው። (ሚክ. 4:3) የብዙዎችን ሕይወት በሚቀጥፈው በጦርነት ከመካፈል ይልቅ ሰዎችን ስለ እውነተኛው አምላክና ስለ ዓላማዎቹ በማስተማር “እውነተኛ የሆነውን ሕይወት” እንዲያገኙ እየረዱ ነው። (1 ጢሞ. 6:19) የቤተሰባቸው አባላት ይቃወሟቸው ይሆናል፤ ወይም ደግሞ የአምላክን መንግሥት በመደገፋቸው የተነሳ የኢኮኖሚ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል። ያም ቢሆን ይሖዋ ምንጊዜም የሚያስፈልጋቸውን ነገር ይሰጣቸዋል። (ማቴ. 6:25, 30-33፤ ሉቃስ 18:29, 30) እነዚህ ነገሮች የአምላክ መንግሥት እውን እንደሆነና የይሖዋን ዓላማ ማስፈጸሙን እንደሚቀጥል ያረጋግጡልናል።

ግሩም ተስፋ ተዘርግቶልናል

14-15. ይሖዋ ሞትን ለዘላለም እንደሚያጠፋ የገባው ቃል የሚፈጸመው እንዴት ነው?

14 ኢየሱስ አሁን በሰማይ ሥልጣኑን ይዟል፤ በመሆኑም ይሖዋ የሰጣቸውን ተስፋዎች በሙሉ ይፈጽማል። (2 ቆሮ. 1:20) ኢየሱስ ከ1914 አንስቶ ጠላቶቹን ድል እያደረገ ይገኛል። (መዝ. 110:1, 2) እሱና ተባባሪ ገዢዎቹ በቅርቡ ክፉዎችን በሙሉ በማጥፋት ድላቸውን ያጠናቅቃሉ።—ራእይ 6:2

15 በኢየሱስ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት ሙታን ይነሳሉ፤ እንዲሁም ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች ወደ ፍጽምና ደረጃ ይደርሳሉ። ከመጨረሻው ፈተና በኋላ ይሖዋ ‘ጻድቃን ናቸው’ ብሎ የሚፈርድላቸው ሰዎች “ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።” (መዝ. 37:10, 11, 29) በጣም ደስ የሚለው ደግሞ “የመጨረሻው ጠላት፣ ሞት ይደመሰሳል።”—1 ቆሮ. 15:26

16. ይሖዋን ለማገልገል የሚያነሳሳን ዋነኛ ምክንያት ምን ሊሆን ይገባል?

16 እስካሁን እንደተመለከትነው፣ የዘላለም ሕይወት ተስፋችን በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ አስተማማኝ ተስፋ ነው። ይህ ተስፋ በእነዚህ አስጨናቂ የመጨረሻ ቀናት ታማኝነታችንን እንድንጠብቅ ይረዳናል። ይሁንና ይሖዋን ማስደሰት ከፈለግን፣ እሱን ለማገልገል የሚያነሳሳን ዋነኛ ምክንያት የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ያለን ፍላጎት ሊሆን አይገባም። ለይሖዋና ለኢየሱስ ታማኝ እንድንሆን የሚያነሳሳን ለእነሱ ያለን ጥልቅ ፍቅር ነው። (2 ቆሮ. 5:14, 15) እንዲህ ያለው ፍቅር፣ እነሱን ለመምሰልና ስለ ተስፋችን ለሌሎች ለመናገር ያነሳሳናል። (ሮም 10:13-15) ከራስ ወዳድነት ነፃ ስንሆንና ልግስናን ስናዳብር ይሖዋ ለዘላለም ወዳጆቹ እንዲሆኑ የሚፈልጋቸው ዓይነት ሰዎች እንሆናለን።—ዕብ. 13:16

17. ከእኛ የሚጠበቀው ምንድን ነው? (ማቴዎስ 7:13, 14)

17 እኛስ የዘላለም ሕይወት ከሚያገኙት ሰዎች መካከል እንገኝ ይሆን? ይሖዋ ይህን አጋጣሚ እንድናገኝ በር ከፍቶልናል። ከእኛ የሚጠበቀው ወደ ሕይወት ከሚወስደው መንገድ ሳንወጣ መኖር ነው። (ማቴዎስ 7:13, 14ን አንብብ።) ይሁንና ለዘላለም በምንኖርበት ጊዜ ሕይወት ምን ይመስላል? በሚቀጥለው ርዕስ ላይ የዚህን ጥያቄ መልስ እንመለከታለን።

መዝሙር 141 ሕይወት ተአምር ነው

a ለዘላለም ለመኖር ትጓጓለህ? ይሖዋ ስለ ሞት ሳንጨነቅ ለዘላለም የምንኖርበት ጊዜ እንደሚመጣ ቃል ገብቶልናል። ይሖዋ ቃሉን እንደሚጠብቅ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን የምንችልባቸውን አንዳንድ ምክንያቶች በዚህ ርዕስ ውስጥ እንመለከታለን።

b ‘ዘላለም’ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

c የሥዕሉ መግለጫ፦ አንድ አረጋዊ ወንድም ወደፊት ለዘላለም ሲኖር የሚያደርጋቸውን አንዳንድ ነገሮች ሲያስብ።