በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተሞክሮ

ተሞክሮ

ለሁሉም ሰው ርኅራኄ አሳዩ

አንድ ቀን፣ በኒው ዚላንድ የምትኖር አንዲት እህት አንዳችሁ ለሌላው አሳቢነት አሳዩ የሚለውን ቪዲዮ ተመለከተች፤ ቪዲዮው ይሖዋ ለሰዎች ከመራራት ባለፈ ርኅራኄውን በተግባር እንደሚያሳይ ይገልጻል። (ኢሳ. 63:7-9) እህታችን እሷም ለሌሎች ተግባራዊ እርዳታ በመስጠት የተማረችውን ነገር በሥራ ላይ ለማዋል ወሰነች። በዚያው ቀን አስቤዛ ለመግዛት ወጥታ ሳለ ጎዳና ላይ የምትኖር አንዲት ሴት አገኘች፤ ከዚያም ምግብ ልትገዛላት እንደምትችል ለሴትየዋ ነገረቻት። እሷም ግብዣዋን ተቀበለች። እህታችን ምግቡን ይዛ ስትመለስ መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል? የተባለውን ትራክት ተጠቅማ አጠር ያለ ምሥክርነት ሰጠቻት።

በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ማልቀስ ጀመረች። በልጅነቷ የይሖዋ ምሥክር የነበረች ቢሆንም ከብዙ ዓመታት በፊት እውነትን እንደተወች ነገረቻት። ሆኖም ወደ እሱ ለመመለስ እንዲረዳት ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀምራ ነበር። እህታችን ለሴትየዋ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠቻት ከመሆኑም ሌላ ጥናት እንድትጀምር ዝግጅት አደረገችላት። a

እኛም ዘመዶቻችንን እንዲሁም በጉባኤ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ጨምሮ ለሁሉም ሰው ርኅራኄ በማሳየት ይሖዋን መምሰል እንችላለን። በተጨማሪም ለሌሎች ለመመሥከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን በመፈለግ ርኅራኄ ማሳየት እንችላለን።

a የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን መርዳት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በሰኔ 2020 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ወደ እኔ ተመለሱ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።