በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጥናት ፕሮጀክት

ታማኝ ሰዎች ስእለታቸውን ይፈጽማሉ

ታማኝ ሰዎች ስእለታቸውን ይፈጽማሉ

መሳፍንት 11:30-40ን አንብብ፤ ከዚያም ስለ ዮፍታሔና ስለ ሴት ልጁ ከሚገልጸው ዘገባ ስእለት መፈጸምን በተመለከተ ምን ትምህርት እንደምናገኝ ለማስተዋል ሞክር።

አውዱን መርምር። ታማኝ የሆኑ እስራኤላውያን ለይሖዋ ስለሚገቡት ስእለት ምን ይሰማቸው ነበር? (ዘኁ. 30:2) ዮፍታሔና ልጁ በይሖዋ ላይ እምነት እንዳላቸው ያሳዩት እንዴት ነው?—መሳ. 11:9-11, 19-24, 36

በጥልቀት ምርምር አድርግ። ዮፍታሔ ስእለቱን የተሳለው ምን በአእምሮው ይዞ ሊሆን ይችላል? (w16.04 7 አን. 12) ስእለቱን ለመፈጸም እሱም ሆነ ልጁ የትኞቹን መሥዋዕቶች ከፍለዋል? (w16.04 7-8 አን. 14-16) በዛሬው ጊዜ ክርስቲያኖች ምን ዓይነት ስእለቶችን ሊሳሉ ይችላሉ?—w17.04 5-8 አን. 10-19

ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ‘ራሴን ስወስን የተሳልኩትን ስእለት መፈጸም የምችለው እንዴት ነው?’ (w20.03 13 አን. 20)

  • ‘ይሖዋን ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ለማገልገል ስል የትኞቹን መሥዋዕቶች መክፈል እችላለሁ?’

  • ‘የጋብቻ ስእለቴን ለመፈጸም ያለኝን ቁርጠኝነት ማጠናከር የምችለው እንዴት ነው?’ (ማቴ. 19:5, 6፤ ኤፌ. 5:28-33)