መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ኅዳር 2018

ይህ እትም ከታኅሣሥ 31, 2018 እስከ የካቲት 3, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

‘እውነትን ግዛ፤ ፈጽሞም አትሽጠው’

እውነትን መግዛት ሲባል ምን ማለት ነው? እውነትን አንዴ ከገዛን በኋላ ፈጽሞ እንዳናጣው ምን ማድረግ ይኖርብናል?

“በእውነትህ እሄዳለሁ”

ይሖዋ ያስተማረንን ውድ እውነት ፈጽሞ ላለማጣት ያደረግነውን ቁርጥ ውሳኔ ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው?

በይሖዋ በመታመን በሕይወት ኑሩ!

የዕንባቆም መጽሐፍ ችግሮች ቢደርሱብንም ውስጣዊ ሰላም ማግኘት እንድንችል ይረዳናል።

አስተሳሰባችሁን የሚቀርጸው ማን ነው?

በሰው ሳይሆን በይሖዋ አስተሳሰብ መቀረጽ የምትችሉት እንዴት ነው?

የይሖዋ ዓይነት አስተሳሰብ ለማዳበር ጥረት እያደረጋችሁ ነው?

‘አእምሮን ማደስ’ ሲባል ምን ማለት ነው? እንዲህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

ደግነት—በቃልና በተግባር የሚገለጽ ባሕርይ

ደግነት፣ የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ፍሬ አንዱ ገጽታ ነው። ይህን ማራኪ ባሕርይ ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት “በጎ አድራጊዎች” በማለት የገለጻቸው ሰዎች እነማን ነበሩ? ይህ የማዕረግ ስም የተሰጣቸውስ ለምንድን ነው?

ለይሖዋ ምን መስጠት እንችላለን?

በምሳሌ 3:9 ላይ የተጠቀሱት “ውድ ነገሮች” ምንድን ናቸው? እነዚህን ነገሮች ተጠቅመን እውነተኛውን አምልኮ መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?