በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለይሖዋ ምን መስጠት እንችላለን?

ለይሖዋ ምን መስጠት እንችላለን?

በአንድ ወቅት ኢየሱስ “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል” በማለት ተናግሮ ነበር። (ሥራ 20:35) ይህ መሠረታዊ እውነት ከይሖዋ ጋር ካለን ዝምድና ጋር በተያያዘም ይሠራል። እንዴት? ይሖዋ ደስተኛ እንድንሆን የሚያደርጉንን ብዙ ስጦታዎች ሰጥቶናል፤ ይሁን እንጂ በመቀበል ከምናገኘው የበለጠ ደስታ ማግኘት የምንችለው ለይሖዋ ስንሰጥ ነው። ታዲያ ለይሖዋ ምን መስጠት እንችላለን? ምሳሌ 3:9 “ባሉህ ውድ ነገሮች . . . ይሖዋን አክብር” ይላል። ካሉን “ውድ ነገሮች” መካከል ጊዜያችን፣ ተሰጥኦዋችን፣ ጉልበታችንና ቁሳዊ ንብረታችን ይገኙበታል። እነዚህን ነገሮች ተጠቅመን እውነተኛውን አምልኮ በመደገፍ ለይሖዋ መስጠት የምንችል ሲሆን ይህም ከፍተኛ ደስታ ያስገኝልናል።

ታዲያ ከቁሳዊ ንብረታችን ጋር በተያያዘ ለይሖዋ መስጠትን ቸል እንዳንል ምን ሊረዳን ይችላል? ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች፣ መዋጮ የሚያደርጉት “የተወሰነ ገንዘብ [እንዲያስቀምጡ]” ነግሯቸው ነበር። (1 ቆሮ. 16:2) በአካባቢህ መዋጮ ማድረግ የሚቻልባቸውን መንገዶች በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ምን ማድረግ ትችላለህ? እባክህ ከታች ያለውን ሣጥን ተመልከት።