በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ምቹ ሁኔታ ፍጠር

ምቹ ሁኔታ ፍጠር

ከግል ጥናትህ ይበልጥ ጥቅም ማግኘት ትፈልጋለህ? የሚከተሉት ምክሮች ለመማር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ይረዱሃል፦

  • ተስማሚ ቦታ ምረጥ። የሚቻል ከሆነ፣ ያልተዝረከረከ እና በቂ ብርሃን ያለው ቦታ ፈልግ። ዴስክ ወይም ጠረጴዛ ጋ መቀመጥ ወይም ደጅ ያለ አመቺ ቦታ መምረጥ ትችላለህ።

  • ብቻህን ሁን። ኢየሱስ ለመጸለይ “በማለዳ . . . ገለል ወዳለ ስፍራ” ሄዷል። (ማር. 1:35) ብቻህን መሆን የማትችል ከሆነ የጥናት ፕሮግራምህን ለቤተሰቦችህ ወይም አብረውህ ለሚኖሩ ሰዎች በማሳወቅ እንዳይረብሹህ ልትጠይቃቸው ትችላለህ።

  • ትኩረትህን ሰብስብ። ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግድ። ለጥናት የምትጠቀመው ስልክህን ወይም ታብሌትህን ከሆነ የመልእክቶቹን ድምፅ ወይም ኔትወርኩን አጥፋ። ማድረግ ያለብህ ነገር እንዳለ ትዝ ካለህ ደግሞ በኋላ እንዳትረሳው ማስታወሻ ላይ ጻፈውና ጥናትህን ቀጥል። ትኩረትህን መሰብሰብ ከከበደህ ጥናትህን ቆም አድርገህ በእግርህ ተንሸራሸር ወይም ሰውነትህን አሳስብ።