መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ነሐሴ 2019

ይህ እትም ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 27, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

“ተስፋ አንቆርጥም”!

ስለ ወደፊቱ ጊዜ ያለን ተስፋ ፈጽሞ ተስፋ እንዳንቆርጥ ሊያጠነክረን የሚችለው እንዴት ነው?

ፍቅራችሁ እየጨመረ ይሂድ

ለፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች የተጻፈው ደብዳቤ፣ ተፈታታኝ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜም እንኳ ፍቅራችን እየጨመረ እንዲሄድ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል።

“የሚሰሙህ” ሰዎች ይድናሉ

የቤተሰባችን አባላት ስለ ይሖዋ እንዲያውቁ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?

አዲስ የአገልግሎት ምድብን መልመድ

ብዙዎች የሚወዱትን የአገልግሎት ምድብ ትተው መሄድ በጣም ይከብዳቸዋል። ለውጡን ለመልመድ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

እምነት—በመንፈሳዊ የሚያጠነክር ባሕርይ

እምነት ታላቅ ኃይል አለው። እምነት እንደ ተራራ ያሉ ከባድ ችግሮችን በጽናት ለመወጣት ይረዳናል።

የመጥምቁ ዮሐንስ ታሪክ ደስታን ጠብቆ ስለ መኖር ምን ያስተምረናል?

ያልጠበቅናቸው ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜም እንኳ ደስታችንን ጠብቀን መኖር የምንችለው እንዴት ነው?