መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ግንቦት 2018

ይህ እትም ከሐምሌ 9 እስከ ነሐሴ 5, 2018 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

የሕይወት ታሪክ

ከድህነት ወደ ብልጽግና

ሳሙኤል ኸርድ ያደገው በድህነት ቢሆንም ፈጽሞ ባልጠበቀው መንገድ በመንፈሳዊ ባለጸጋ መሆን ችሏል።

ሰላም ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

የምንኖረው ሁከት በነገሠበት ዓለም ውስጥ በመሆኑ ሰላማዊ ሕይወት ለመምራት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። የአምላክ ቃል በዚህ ረገድ ሊረዳን ይችላል።

ይሖዋ “በጽናት ፍሬ የሚያፈሩ” ሰዎችን ይወዳል

አብዛኞቹ ሰዎች ምሥራቹን በማይቀበሉበት ክልል ውስጥ መስበክ ተስፋ አስቆራጭ ሊሆንብን ይችላል። ይሁንና ሁላችንም በአገልግሎታችን ፍሬያማ መሆን እንችላለን።

‘ብዙ ፍሬ ማፍራታችንን’ መቀጠል ያለብን ለምንድን ነው?

የምንሰብክበትን ምክንያት ምንጊዜም ማስታወሳችን አስፈላጊ ነው።

ጠላታችሁን እወቁ

ሰይጣን የሚያሳድረውን ተጽዕኖ እና የሚሸርበውን ተንኮል እናውቃለን።

ወጣቶች—ዲያብሎስን ተቋቋሙ

ሁላችንም በመንፈሳዊ ውጊያ ላይ ነን። በተለይ ደግሞ ወጣት ክርስቲያኖች በውጊያው በቀላሉ የሚሸነፉ መስለው ሊታዩ ይችላሉ፤ ሆኖም ለጦርነት የሚያስፈልጋቸውን የጦር ትጥቅ ለብሰዋል።

የተትረፈረፈ ምርት

ዩክሬን ውስጥ ባለ አንድ አካባቢ ከነዋሪዎቹ አንድ አራተኛ የሚሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው!