በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በ2012 በንዥንያ አፕሻ፣ ዩክሬን የተደረገ የአውራጃ ስብሰባ

የተትረፈረፈ ምርት

የተትረፈረፈ ምርት

ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ በዚህ የፍጻሜ ዘመን የተትረፈረፈ ምርት እንደሚያገኙ ትንቢት ተናግሮ ነበር። (ማቴ. 9:37፤ 24:14) ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት ዩክሬን ውስጥ በሚገኝ ትራንስካርፔቲያ የተባለ አካባቢ ልዩ በሆነ መንገድ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት እንደሆነ እንመልከት። በዚያ አካባቢ በሚገኙ ሦስት አጎራባች ከተሞች ውስጥ ብቻ 50 ጉባኤዎችና ከ5,400 በላይ አስፋፊዎች አሉ። * እንዲያውም በሦስቱ ከተሞች ውስጥ ያለው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት ከይሖዋ ምሥክሮች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከአራት ሰዎች አንዱ የይሖዋ ምሥክር ነው!

በእነዚህ ከተሞች ውስጥ ያለው የአገልግሎት ክልል ምን ይመስላል? በዚያ የሚኖር ቫሲሌ የሚባል አንድ ወንድም እንዲህ ብሏል፦ “ሰዎቹ ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ያላቸው ሲሆን የፍትሕ ጉዳይም በጣም ያሳስባቸዋል፤ በቤተሰብ አባላት መካከል የጠበቀ ወዳጅነት ያለ ከመሆኑም ሌላ ነዋሪዎቹ እርስ በርስ ለመረዳዳት ከልብ ይጥራሉ። እርግጥ በምናምንባቸው ነገሮች የሚስማሙት ሁልጊዜ አይደለም። ይሁን እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ ሐሳብ ስናሳያቸው በጥሞና ያዳምጣሉ።”

እርግጥ ነው፣ ወንድሞችና እህቶች የአስፋፊው ቁጥር ከጠቅላላው ነዋሪ ቁጥር ጋር በጣም ተቀራራቢ በሆነበት እንደዚህ ባለ አካባቢ ሲሰብኩ አንዳንድ ያልተለመዱ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በአንዱ ጉባኤ ውስጥ ያሉት አስፋፊዎች ብዛት 134 ሲሆን በክልሉ ውስጥ ያሉት የግል ቤቶች ግን 50 ብቻ ናቸው! ታዲያ አስፋፊዎቹ ይህን ተፈታታኝ ሁኔታ መወጣት የቻሉት እንዴት ነው?

ብዙ ወንድሞችና እህቶች፣ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉባቸው አካባቢዎች ሄደው ለመስበክ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ዮናሽ የሚባሉ አንድ የ90 ዓመት አረጋዊ ወንድም እንዲህ ብለዋል፦ “በጉባኤያችን ያሉት አስፋፊዎች ቁጥር፣ በክልሉ ካሉት ቤቶች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ለአንድ አስፋፊ የሚደርሰው ሁለት ቤት ብቻ ነው። አሁን ጤንነቴ በማሽቆልቆሉ የምሰብከው በመንደራችን ውስጥ ነው፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ለየትኛውም ጉባኤ ያልተመደበ ክልል እየሄድኩ በሃንጋሪያኛ ቋንቋ እሰብክ ነበር።” አስፋፊዎች ወደ ሌሎች ክልሎች ሄደው ለመመሥከር የራሳቸውን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ አስፈልጓቸዋል። ወንድም ዮናሽ እንዲህ ብለዋል፦ “ባቡር ለመያዝ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እነሳ ነበር፤ ከዚያም እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ካገለገልኩ በኋላ ባቡር ተሳፍሬ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ። በየሳምንቱ ሁለት ወይም ሦስት ቀናት እንዲህ አደርግ ነበር።” ታዲያ እኚህ ወንድም ልፋታቸው የማያስቆጭ እንደሆነ ይሰማቸዋል? እንዲህ ብለዋል፦ “እንዲህ ባለው አገልግሎት መካፈሌ ታላቅ ደስታ አስገኝቶልኛል። ምንም ጉባኤ በሌለበት ቦታ የሚኖር አንድ ቤተሰብ እውነትን እንዲማር የመርዳት ልዩ መብትም አግኝቻለሁ።”

በዚህ አካባቢ ባሉ ጉባኤዎች ውስጥ ያሉ ሁሉም ክርስቲያኖች ረጅም ርቀት ተጉዘው መስበክ እንደማይችሉ የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ አረጋውያንን ጨምሮ ሁሉም አስፋፊዎች የጉባኤያቸውን ክልል አጣርተው ለመሸፈን ይጥራሉ። በዚህም የተነሳ በ2017 በእነዚህ ሦስት ከተሞች ውስጥ በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ ሰዎች ቁጥር፣ የአስፋፊዎቹን ቁጥር እጥፍ የነበረ ሲሆን ይህም ከጠቅላላው ነዋሪ ግማሹ ማለት ነው። በእርግጥም፣ የምናገለግለው የትም ይሁን የት ‘የጌታ ሥራ የበዛልን’ መሆን እንችላለን።—1 ቆሮ. 15:58

^ አን.2 የከተሞቹ ስም ህልቦክይ ፖቲክ፣ ሰረድንያ ቮዲያና እና ንዥንያ አፕሻ ነው።