በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጥናት ፕሮጀክት

የፍትሕ መጓደልን በጽናት መቋቋም

የፍትሕ መጓደልን በጽናት መቋቋም

ዘፍጥረት 37:23-28፤ 39:17-23ን አንብብ፤ ከዚያም ዮሴፍ የደረሰበትን የፍትሕ መጓደል የተቋቋመው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

አውዱን መርምር። ዮሴፍ የፍትሕ መጓደል የደረሰበት ለምንድን ነው? (ዘፍ. 37:3-11፤ 39:1, 6-10) ዮሴፍ የደረሰበትን የፍትሕ መጓደል መቋቋም ያስፈለገው ለምን ያህል ጊዜ ነው? (ዘፍ. 37:2፤ 41:46) በዚያ ወቅት ይሖዋ ለዮሴፍ ምን አድርጎለታል? ምንስ አላደረገለትም?—ዘፍ. 39:2, 21w23.01 17 አን. 13

በጥልቀት ምርምር አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዮሴፍ የጶጢፋር ሚስት ለሰነዘረችበት የሐሰት ክስ ምንም ዓይነት የመከላከያ መልስ እንደሰጠ አይናገርም። የሚከተሉት ጥቅሶች፣ ዮሴፍ ዝም ለማለት የመረጠው ለምን እንደሆነ ወይም ሁሉም ዝርዝር ጉዳዮች ዘገባው ላይ እንዲካተቱ መጠበቅ የሌለብን ለምን እንደሆነ ለማስተዋል የሚረዱን እንዴት ነው? (ምሳሌ 20:2፤ ዮሐ. 21:25፤ ሥራ 21:37) ዮሴፍ የደረሰበትን የፍትሕ መጓደል በጽናት እንዲቋቋም የረዱት የትኞቹ ባሕርያት ሊሆኑ ይችላሉ?—ሚክ. 7:7፤ ሉቃስ 14:11፤ ያዕ. 1:2, 3

ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ‘የኢየሱስ ደቀ መዝሙር እንደመሆኔ መጠን ምን ዓይነት የፍትሕ መጓደል እንደሚደርስብኝ መጠበቅ ይኖርብኛል?’ (ሉቃስ 21:12, 16, 17፤ ዕብ. 10:33, 34)

  • ‘የሚደርስብኝን የፍትሕ መጓደል በተሳካ ሁኔታ ለመቋቋም መዘጋጀት የምችለው እንዴት ነው?’ (መዝ. 62:7, 8፤ 105:17-19w19.07 2-7)