በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወንድም ኬኔዝ ኩክና ባለቤቱ ጄሚ

አዲስ የበላይ አካል አባል

አዲስ የበላይ አካል አባል

ረቡዕ ጥር 24, 2018 በዩናይትድ ስቴትስና በካናዳ የሚገኙት የቤቴል ቤተሰብ አባላት ወንድም ኬኔዝ ኩክ የበላይ አካል አባል ሆኖ እንደተሾመ የሚገልጽ አስደሳች ማስታወቂያ ተነገራቸው።

ወንድም ኩክ ተወልዶ ያደገው በማዕከላዊ ደቡብ ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ ከጥቂት ጊዜ በፊት፣ አብሮት ከሚማር አንድ ልጅ እውነትን ሰማ፤ ከዚያም ሰኔ 7, 1980 ተጠመቀ። መስከረም 1, 1982 የዘወትር አቅኚ በመሆን የሙሉ ጊዜ አገልግሎቱን ጀመረ። ለሁለት ዓመት በአቅኚነት ካገለገለ በኋላ ወደ ቤቴል ተጠራ። የቤቴል አገልግሎቱን የጀመረው ጥቅምት 12, 1984 በዎልኪል፣ ኒው ዮርክ ነበር።

ወንድም ኩክ በቀጣዮቹ 25 ዓመታት በሕትመት ክፍል እንዲሁም በቤቴል ቢሮ ውስጥ በተለያዩ የሥራ ምድቦች አገልግሏል። በ1996 ጄሚ ከተባለች እህት ጋር ትዳር መሠረተ፤ እሷም ቤቴል ገብታ በዎልኪል አብራው ማገልገል ጀመረች። ታኅሣሥ 2009 ወንድም ኩክና ባለቤቱ በፓተርሰን፣ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የትምህርት ማዕከል የተዛወሩ ሲሆን በዚያም ወንድም ኩክ በደብዳቤ ልውውጥ ክፍል ውስጥ እንዲያገለግል ተመደበ። ሚያዝያ 2016 ወንድም ኩክና ባለቤቱ ለአጭር ጊዜ ያህል ወደ ዎልኪል ከተመለሱ በኋላ ወደ ብሩክሊን፣ ኒው ዮርክ ተዛወሩ። ከአምስት ወር በኋላ በዎርዊክ፣ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ተዛውረው ማገልገል ጀመሩ። ጥር 2017 ወንድም ኩክ የበላይ አካሉ የጽሑፍ ዝግጅት ኮሚቴ ረዳት ሆኖ ተሾመ።