በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

የወንድሞቻችንን እና የእህቶቻችንን የሕይወት ታሪክ ማንበብ ትወዳለህ?

በየማለዳው አንድ የሕይወት ታሪክ የሚያነቡ ባልና ሚስት እንዲህ ብለዋል፦ “ከእነዚህ ታሪኮች የምናገኘው ደስታና ማበረታቻ ልዩ ነው! ምንም ዓይነት ሁኔታ ቢያጋጥመን ታማኝ መሆን እንደምንችል ያስታውሱናል።” አንዲት እህት ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “እነዚህ የሕይወት ታሪኮች ያጽናኑናል፣ ያበረታቱኛል እንዲሁም ልቤ በጥልቅ እንዲነካ ያደርጋሉ። ወንድሞቻችንንና እህቶቻችን ዓላማ ያለው ሕይወት እንደሚመሩ እንድገነዘብ ያደርጉኛል። ታሪካቸው በአገልግሎት የማደርገውን ተሳትፎ እንድጨምር ያነሳሳኛል፤ እንዲሁም ልጆቼን ይሖዋን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዲያገለግሉት እንድረዳቸው ያበረታታኛል።”

የሕይወት ታሪኮች መንፈሳዊ ግቦች እንድታወጣ፣ ደካማ ጎንህን እንድታሻሽል እንዲሁም ከባድ ችግሮችን በደስታ እንድትወጣ ይረዱሃል። እነዚህን የሕይወት ታሪኮች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

  • jw.org ወይም JW Library® ላይ ተከታታይ ርዕሶች በሚለው ዓምድ ሥር “የይሖዋ ምሥክሮች የሕይወት ታሪኮች” የሚለውን ተመልከት።

  • “የይሖዋ ምሥክሮች የሕይወት ታሪኮችን” መጠበቂያ ግንብ ላይም ማግኘት ትችላለህ። በታኅሣሥ የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ “ርዕስ ማውጫ” በሚለው ርዕስ ሥር “የሕይወት ታሪኮች” የሚለውን ተመልከት።