በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ለግል ጥናት እና ለቤተሰብ አምልኮ የሚረዱ ሐሳቦች

ለግል ጥናት እና ለቤተሰብ አምልኮ የሚረዱ ሐሳቦች

ይሖዋን የምናመልከው በጉባኤ፣ በወረዳና በክልል ስብሰባዎች ላይ ተሰብስበን ብቻ ሳይሆን በግልና በቤተሰብ ደረጃም ጭምር ነው። ለግል ጥናትና ለቤተሰብ አምልኮ የሚረዱ አንዳንድ ሐሳቦችን እስቲ እንመልከት፦

  • ለጉባኤ ስብሰባዎች ተዘጋጁ። መዝሙሮቹን መለማመድ እንዲሁም ሁሉም የቤተሰባችሁ አባላት መልስ እንዲዘጋጁ መርዳት ትችላላችሁ።

  • አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ አንብቡ። ከዚያም ዘገባውን በሥዕል ለማስቀመጥ ወይም ያገኛችሁትን ትምህርት ለመጻፍ ሞክሩ።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝን አንድ ጸሎት መርምሩ፤ ከዚያም የጸሎታችሁን ይዘት ለማሻሻል የሚረዳችሁ እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።

  • አንድ ቲኦክራሲያዊ ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም ከሌሎች ጋር ተወያዩበት ወይም ከቪዲዮው ያገኛችሁትን ትምህርት ጻፉ።

  • ለአገልግሎት ተዘጋጁ፤ ምናልባትም የልምምድ ፕሮግራም ማዘጋጀት ትችሉ ይሆናል።

  • ፍጥረትን ተመልከቱ፤ ከዚያም ስለ ይሖዋ ስላገኛችሁት ትምህርት አሰላስሉ ወይም ተወያዩ። a

a በመጋቢት 2023 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ፍጥረትን በማየት ስለ ይሖዋ ይበልጥ ተማሩ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።