መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥቅምት 2019

ይህ እትም ከታኅሣሥ 2-29, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

1919—የዛሬ መቶ ዓመት

በ1919 ይሖዋ፣ የስብከቱን ሥራ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሕዝቦቹን አበረታቷቸዋል። በመጀመሪያ ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ ትልቅ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር።

አምላክ የፍርድ እርምጃ ሲወስድ ሁልጊዜ በቂ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል?

ይሖዋ አምላክ፣ እየመጣ ስላለው እንደ አውሎ ነፋስ ያለ አደጋ የምድርን ነዋሪዎች እያስጠነቀቀ ነው፤ ይህ “አውሎ ነፋስ” ሰዎች በአየር ትንበያ ዘገባዎች ላይ ከሚሰሟቸው አደጋዎች ሁሉ የከፋ ነው። ለመሆኑ ይሖዋ ሰዎችን እያስጠነቀቀ ያለው እንዴት ነው?

“በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ሥራ የበዛላችሁ ሁኑ

“በመጨረሻዎቹ ቀናት” ማብቂያ ላይ የትኞቹ ክንውኖች ይፈጸማሉ? እነዚህን ክንውኖች እየተጠባበቅን ባለንበት በዛሬው ጊዜስ ይሖዋ ምን እንድናደርግ ይጠብቅብናል?

‘በታላቁ መከራ’ ወቅት ታማኝነታችሁን ጠብቁ

ይሖዋ ‘በታላቁ መከራ’ ወቅት ምን እንድናደርግ ይጠብቅብናል? በታላቁ መከራ ወቅት ታማኝ ለመሆን ከአሁኑ ራሳችንን ማዘጋጀት የምንችለውስ እንዴት ነው?

ይሖዋ ምን እንድትሆን ያደርግሃል?

በጥንት ዘመን ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያደረገ ከመሆኑም ሌላ ኃይል ሰጥቷቸው ነበር። በዛሬው ጊዜስ ይሖዋ እሱን ለማገልገል ብቁ የሚያደርገን እንዴት ነው?

ይሖዋን ብቻ አምልኩ

የምናመልከው ይሖዋን ብቻ መሆን አለመሆኑን ማወቅ እንድንችል ጉዳዩን ከሁለት አቅጣጫዎች አንጻር እንመርምር።