ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
በግንዛቤያችን ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎችን መከታተል የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን ግንዛቤ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እያጠራ ባለበት በዚህ ዘመን መኖር እንዴት ያለ ታላቅ መብት ነው! (ዳን. 12:4) ያም ቢሆን፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ባለን ግንዛቤ ላይ የተደረጉትን ማስተካከያዎች መከታተል ከባድ ሊሆንብን ይችላል። እነዚህን ማስተካከያዎችና ማብራሪያቸውን ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?
• የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮች በርዕሰ ጉዳይ የተከፋፈለ አጠር ያለ ዝርዝር ይዟል። “የይሖዋ ምሥክሮች” በሚለው ክፍል ውስጥ “አመለካከት እና እምነት” በሚለው ሥር ያለውን “ስለምናምንባቸው ነገሮች ያገኘነው አዲስ ግንዛቤ” የሚል ክፍል ተመልከት።
• የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ (እንግሊዝኛ) ላይ ያለው “ስለምናምንባቸው ነገሮች ያገኘነው አዲስ ግንዛቤ (Beliefs Clarified)” የሚለው ክፍል እስካሁን የተደረጉትን ማስተካከያዎች በሙሉ በዓመት በዓመት ከፋፍሎ ይዘረዝራል። የርዕሰ ጉዳዮቹን ዝርዝር ለማግኘት ዎችታወር ላይብረሪ (እንግሊዝኛ) ወይም የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት የመፈለጊያ ሣጥን ላይ “understanding clarified” (ትእምርተ ጥቅሱንም ጨምሮ) ብለህ ጻፍ።
በቅርቡ የተደረገ አንድ ማስተካከያ መርጠህ አሁን ያለንን ግንዛቤ እና ማስተካከያው የተደረገበትን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያት በግል ጥናትህ ላይ ለመመርመር ለምን አትሞክርም?