በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ

3 | ከሌሎች ጋር ያለህ ግንኙነት

3 | ከሌሎች ጋር ያለህ ግንኙነት

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ሰዎች በዓለም ላይ በሚከሰተው ቀውስ ሲጨነቁ ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ይሻክራል።

  • ሰዎች ራሳቸውን ከጓደኞቻቸው ያገልላሉ።

  • በባልና ሚስት መካከል የሚፈጠረው ግጭት ይጨምራል።

  • ወላጆች የልጆቻቸውን ጭንቀት ሳያስተውሉ ይቀራሉ።

ማወቅ ያለብህ ነገር

  • ከሌሎች ጋር የምትመሠርተው ወዳጅነት ለአካላዊም ሆነ ለስሜታዊ ደህንነትህ በጣም አስፈላጊ ነው፤ በተለይ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ።

  • ዓለም ላይ የሚከሰቱት ቀውሶች የሚፈጥሩት ውጥረት ባላሰብከው መንገድ የቤተሰብ ሕይወትህን ሊፈታተነው ይችላል።

  • መጥፎ ዜናዎች ልጆችህን ከምታስበው በላይ ሊረብሿቸው ይችላሉ።

አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17

በችግር ጊዜ ከጎንህ የሚቆም እንዲሁም ጠቃሚ ምክር የሚሰጥህ ወዳጅ አለህ? እስቲ ይህን ወዳጅህን ለማሰብ ሞክር። ከልቡ የሚያስብልህ ሰው ከጎንህ እንዳለ ማወቅህ በራሱ የሕይወትን ፈተና ለማሸነፍ አቅም ይሰጥሃል።