በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማስተዋወቂያ

ማስተዋወቂያ

ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮች

ብዙውን ጊዜ አንድ ቤተሰብ ስኬታማ ሳይሆን የቀረው ለምን እንደሆነ ሲነገር እንሰማለን። በአንጻሩ ግን አንዳንድ ቤተሰቦች ስኬታማ ሊሆኑ የቻሉት ለምንድን ነው?

  • በዩናይትድ ስቴትስ፣ በ1990 እና በ2015 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፍቺ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፍቺ ቁጥር ደግሞ በሦስት እጥፍ ጨምሯል።

  • ወላጆች ግራ ገብቷቸዋል፤ አንዳንድ ባለሙያዎች ‘ልጆች ምንም አደረጉ ምን እነሱን ማበረታታት አስፈላጊ ነው’ በማለት ይመክራሉ፤ ሌሎች ደግሞ አንድ አፍቃሪ ወላጅ በልጆቹ ላይ ጥብቅ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ።

  • ወጣቶች ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች ሳይማሩ ያድጋሉ።

ሐቁ ግን የሚከተለው ነው፦

  • ትዳር አስደሳችና ዘላቂ ጥምረት መሆን ይችላል።

  • ወላጆች ልጆቻቸውን በፍቅር መቅጣት የሚችሉበትን መንገድ ሊማሩ ይችላሉ።

  • ወጣቶች አዋቂ ሲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች ከልጅነታቸው መማር ይችላሉ።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? ይህ ንቁ! መጽሔት ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮችን ያብራራል።