በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | የቋንቋ ልዩነትመሰናክሎቹና መፍትሔው

ከጥንት ጀምሮ የነበረውን መሰናክል ማለፍ

ከጥንት ጀምሮ የነበረውን መሰናክል ማለፍ

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ 7,000 ያህል ቋንቋዎች አሉ፤ የእነዚህ ቋንቋዎች ብዛትና የቋንቋዎቹ ባሕርይ መለያየት ጉዞ፣ ንግድ፣ ትምህርትና አስተዳደር አስቸጋሪ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል። ይህ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ችግር ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በ475 ዓ.ዓ. ገደማ ፋርሳውያን በንጉሥ አሐሽዌሮስ (ቀዳማዊ ጠረክሲስ ሳይሆን አይቀርም) አገዛዝ ሥር ንጉሣዊ አዋጆችን በፋርስ ግዛት ለነበሩት ሕዝቦች አስተላልፈዋል፤ “ከሕንድ አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ ላሉት 127 አውራጃዎች . . . ጻፉ፤ ለእያንዳንዱ አውራጃ በራሱ ጽሑፍ፣ ለእያንዳንዱም ሕዝብ በራሱ ቋንቋ ተጻፈለት።” *

በዛሬው ጊዜ አብዛኞቹ ድርጅቶች አልፎ ተርፎም መንግሥታት እንዲህ ዓይነቱን ከባድ ሥራ ሊሠሩት ቀርቶ ሊሞክሩት እንኳ አልቻሉም። ሆኖም ይህን ሥራ በተሳካ ሁኔታ ማከናወን የቻለ አንድ ድርጅት አለ። የይሖዋ ምሥክሮች መጽሔቶችን፣ የኦዲዮ ቪዲዮ ፕሮግራሞችን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ መጻሕፍትን በድምሩ ከ750 በሚበልጡ ቋንቋዎች ያዘጋጃሉ። ይህም 80 የሚያህሉ የምልክት ቋንቋዎችን ይጨምራል። በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክሮች ለዓይነ ስውራን የተለያዩ ጽሑፎችን በብሬይል ያዘጋጃሉ።

የሚያስገርመው ደግሞ የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ሥራ የሚያከናውኑት የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ብለው አለመሆኑ ነው። እንዲያውም ተርጓሚዎቹም ሆኑ ሌሎች ሥራዎችን የሚያከናውኑት ሰዎች በሙሉ ፈቃደኛ ሠራተኞች ናቸው። የይሖዋ ምሥክሮች ጽሑፎችን በበርካታ ቋንቋዎች ለመተርጎም ይህን ያህል ጥረት የሚያደርጉት ለምንድን ነው? የትርጉም ሥራቸውን የሚያከናውኑትስ እንዴት ነው?

^ አን.3 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስቴር 8:9ን ተመልከት።