2 ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን?
ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
በራሳችን ላይ መከራ የምናመጣው እኛው ከሆንን መከራውን መቀነስ የምንችልበት መንገድ ሊኖር ይችላል።
ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች
ከዚህ በታች ለተጠቀሱት መከራዎች መድረስ የሰዎች አስተዋጽኦ ምን ያህል ነው?
-
ጥቃት
የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከ4 አዋቂዎች መካከል 1ዱ በልጅነቱ አካላዊ ጥቃት ደርሶበታል፤ ከ3 ሴቶች መካከል 1ዷ ደግሞ በሕይወቷ ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ አካላዊ ወይም ፆታዊ ጥቃት (አሊያም ሁለቱም) ይደርስባታል።
-
ሞት
የዓለም የጤና ድርጅት ያሳተመው ዎርልድ ኸልዝ ስታትስቲክስ 2018 የተባለ ጽሑፍ እንደገለጸው “በ2016 በዓለም ዙሪያ 477,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።” ይህ አኃዝ በዚያው ዓመት በጦርነት ወይም በእርስ በርስ ግጭት ምክንያት እንደሞቱ የሚገመቱትን 180,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች አይጨምርም።
-
የጤና እክል
ናሽናል ጂኦግራፊክ በተሰኘው መጽሔት ላይ በወጣ አንድ ርዕስ ላይ ፍራን ስሚዝ የተባለች ጸሐፊ እንዲህ ብላለች፦ “ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ትንባሆ ያጨሳሉ፤ ትንባሆ ደግሞ ለሚከተሉት ቀንደኛ የሞት መንስኤ የሆኑ አምስት የጤና እክሎች ያጋልጣል፦ የልብ በሽታ፣ አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ የአየር ቧንቧ መደፈንና የሳንባ ካንሰር።”
-
ኢፍትሐዊነት
የሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ጄ ዋትስ እንዲህ ብለዋል፦ “ድህነት፣ መድልዎ፣ ዘረኝነት፣ ፆታዊ አድልዎ፣ ስደትና ማኅበራዊ ፉክክር ለአእምሮ ጤና መታወክ ያጋልጣሉ።”
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
jw.org ላይ የሚገኘውን አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
በዓለም ላይ ለሚደርሰው አብዛኛው መከራ ተጠያቂዎቹ ሰዎች ናቸው።
አብዛኛው መከራ የሚደርሰው ጨቋኝ የሆኑ መንግሥታት፣ ሊያገለግሉት የሚገባውን ሕዝብ በመበደላቸው ምክንያት ነው።
“ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ ነው።”—መክብብ 8:9
የሚደርስብንን መከራ መቀነስ እንችላለን።
የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ጤንነታችንን ለማሻሻልና ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር ይረዳናል።
“የሰከነ ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ ቅናት ግን አጥንትን ያነቅዛል።”—ምሳሌ 14:30
“የመረረ ጥላቻ፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ ጩኸትና ስድብ ሁሉ እንዲሁም ክፋት ሁሉ ከእናንተ መካከል ይወገድ።”—ኤፌሶን 4:31