በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

4 የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?

4 የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

የዚህ ጥያቄ መልስ ለሕይወት ባለን አመለካከት ላይ ለውጥ ያመጣል።

ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች

ዓለማችንን ውብ አድርጎ የፈጠረው አምላክ በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንመራ ይፈልጋል ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ነው?

ሃይማኖተኛ ያልሆኑ ሰዎች በዓለም ላይ ያለውን መከራ ሲያዩ በአምላክ ባሕርይ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፤ አልፎ ተርፎም እሱ መኖሩን ይጠራጠራሉ። በእነዚህ ሰዎች አመለካከት መሠረት መከራ የሚደርስብን (1) አምላክ መከራን ለማስቆም ኃይል ስለሌለው፣ (2) አምላክ መከራን ማስቆም ስለማይፈልግ ወይም (3) አምላክ ስለሌለ ነው።

ሆኖም ያሉት አማራጮች እነዚህ ብቻ ናቸው?

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

jw.org ላይ የሚገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ የፈጠረን በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር አይደለም።

አምላክ ደስተኛ ሆነን እንድንኖር ይፈልጋል።

“ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ የተሻለ ነገር የለም . . . ደግሞም ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።”መክብብ 3:12, 13

አምላክ አዳምንና ሔዋንን የፈጠራቸው ደስተኛ ሆነው እንዲኖሩ ነበር።

የአምላክ ዓላማ እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው መከራ እንዲደርስባቸው አልነበረም።

“አምላክ ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ ‘ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም።’”ዘፍጥረት 1:28

አዳምና ሔዋን አምላክን ላለመታዘዝ መረጡ።

በመሆኑም በራሳቸውም ሆነ በዘሮቻቸው ላይ ብዙ መከራ አመጡ።

“በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።”ሮም 5:12 *

አምላክ ለሰው ልጆች ከእሱ አገዛዝ ውጭ ሆነው ራሳቸውን የመምራት ችሎታ አልሰጣቸውም።

ውኃ ውስጥ መኖር እንድንችል ተደርገን እንዳልተፈጠርን ሁሉ ራሳችንን መምራት እንድንችል ተደርገንም አልተፈጠርንም።

“[ሰው] አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም።”ኤርምያስ 10:23

አምላክ መከራ እንዲደርስብን አይፈልግም።

አምላክ መከራ ከሚያስከትሉብን ነገሮች በተቻለ መጠን እንድንርቅ ይፈልጋል

“ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው! እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ . . . ይሆናል።”ኢሳይያስ 48:18

^ አን.17 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ኃጢአት” የሚለው ቃል ሰዎች የሚፈጽሙትን መጥፎ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ማለትም በዘር የወረሱትን ኃጢአትም ያመለክታል።