መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥር 2020

ይህ እትም ከመጋቢት 2 እስከ ሚያዝያ 5, 2020 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

“ሂዱና . . . ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”

የ2020 የዓመት ጥቅስ ደቀ መዛሙርት የማድረግ ችሎታችንን በማሻሻል ላይ ትኩረት እንድናደርግ ይረዳናል።

ሌሎችን ‘በእጅጉ ማጽናናት’ ትችላለህ

ሌሎችን ለማጽናናትና ለመደገፍ የሚረዱህን ሦስት ባሕርያት በዚህ ርዕስ ላይ ተመልከት።

በአምላክህ በይሖዋ ፊት ውድ ነህ!

በሕመም፣ በኢኮኖሚ ችግር ወይም በዕድሜ መግፋት የተነሳ መንፈሳችን ሲደቆስ ከሰማያዊው አባታችን ፍቅር ሊለየን የሚችል አንዳች ነገር እንደሌለ መተማመን እንችላለን።

“ይህ መንፈስ ራሱ . . . ይመሠክራል”

አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ መቀባቱን የሚያውቀው እንዴት ነው? አንድ ሰው እንዲህ ዓይነት ጥሪ ሲቀበል ምን ለውጥ ያጋጥመዋል?

ከእናንተ ጋር እንሄዳለን

በመታሰቢያው በዓል ላይ ከቂጣውና ከወይን ጠጁ ለሚወስዱት ሰዎች ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚወስዱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሄድ ይህ ሊያሳስበን ይገባል?